ሴቶች በሁሉም መስክ ፊት በመሠለፍ ውጤታማ ተግባራት ማከናወን እንዳለባቸው ተገለፀ።
የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ሴቶች ውጤታማ የስራ አፈፃፀም እንዲያስመዝገቡ ምን መሥራት ይገባል በሚል ርዕሠ ጉዳይ ከመከላከያ ልዩ ልዩ ስታፍ ክፍሎች ከተውጣጡ የሠራዊት አባላት እና ሲቪል ሴት ሰራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል።

የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ሁሉአገርሽ ድረስ በርካታ የህይወት ውጣ ውረድን አልፈው በሲቪሉ ዓለምም ሆነ በውትድርናው ዓለም የውድድር መድረክ ላይ አልፈው በአመራርነት ደረጃ ላይ የሚገኙት ሴቶችን አርአያ በማድረግ እናንተም ወደ ከፍታው ለመምጣት መገስገስ ይኖርባችኋል ብለዋል።
ውጤት ለማምጣት በመተባበር እና በመደጋገፍ ሊሰራ እንደሚገባ እና በግል መስራት ብቻውን የትም ሊያደርስ እንደማይችል ተነስቷል። ውጤታማ ድጋፍ ሰጭ ሲኖር ጠካራ ግዳጅ መፈፀም የሚችል ሀይል ለማፍራት እንደሚቻልም ከመድረኩ እና ከተሳታፊዎች ሀሳብ ተነስቷል።

የበታቾቹን በዓላማ የሚመራ እንዲሆኑ ልምድ እና ተሞክሮውን እያካፈለ የሰለጠነውን ስልጠና ወደተግባር እየቀየረ ለራሱ እና ለተቋሙ እድገት የራሱን ሚና የሚጫወት አባል ማፍራት አስፈላጊ በመሆኑ በትውልድ ቅብብሎሽ ሂደት ውስጥ ለማለፍ ራስን ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ለለበሱት ዩኒፎርም ተገዥ መሆን በወታደራዊ ዲሲፕሊን መመራት የእርስ በእርስ ግንኙነትን ማጠናከር ለተሰማሩበት ሙያ የሚመጥን ልምድና ችሎታ ማካበት እና ራስን በትምህርት ማሳደግ ውጤታማ የስራ አፈፃፀም ለማስመዝገብ አስፈላጊ ነገሮች መሆናቸው በውይይቱ በሰፊው ተነስቷል።
ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ ዕፀገነት ዴቢሳ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official