የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምንጊዜም መነሻ እና መድረሻ መሠረቱ ኢትዮጵያ ነች፡፡ ኢትዮጵያን ከጠላት መጠበቅ፣ ዘወትር ለሠላሟ መሥራት፣ ለዕድገቷ መታተር ፣ለክብሯና ለነፃነቷ መታገል፣ ለህዝቦቿ አንድነትና ሠላም ዘብ መሆን ፣ብሄራዊ ጥቅሟን ማሥከበር ሁሌም የሚፈፅማቸው የየዕለት ተግባራቶቹ ናቸው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሀገር ላይ እጃቸውን የሚሰነዝሩ የጥፋት ኃይሎችን በብቃት እየመከተ የሚቃጡ ትንኮሳዎችን እያመከነ ሠላምና ልማትን እያሥቀጠለ የሚገኝ የኩሩ ህዝቦች መኖሪያ የህብረ ብሄር ቡቃያ ነው።
ለሀገሩ እና ለሠንደቅ ዓላማው ክብር ሲል ለተልዕኮው ቅድሚያ የሚሠጠው ሠራዊት በየትኛውም ጊዜ የተሠጠውን ተቋማዊና ሀገራዊ ተልዕኮ በድል የተወጣ ፣እየተወጣ የሚገኝ፣ ህዝባዊነቱን የሚያሥቀድም፣ በህዝቦች ልቦና የታተመ ሥለመሆኑ ሁሉንም ያግባባል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮ በሚፈፅምባቸው ቀጠናዎች ሁሉ የህዝብ ድጋፍ ያልተለየው ህብረተሠቡ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ አብሮነቱን የሚገልፅለት በመሆኑ ድልን እየተጎናፀፈ ሠላምና ልማትን እያሠፈነ የሚገኝ ተመራጭ የሠላምና የልማት ኃይል ነው።
ሠውን ለማኖር በሰዋዊ በጎነቱ እስከ ህይወት መስዋዕትነት የሚከፍል ፣ ልጅ ሚስት ቤተሰቡን ትቶ ሁሌም ለሀገር ሠላም ለተሠለፈው፤ የሀገሩን ክብር ለማሥጠበቅ ለሞት ለማያመነታው፣ ለነፃነት ታሪክ ሰሪ ታሪክ አሻጋሪ፣ የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም የሚያሥከብር ኃይል ነው። ታዲያ ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ልናደርግለት የምንችለው ጥቂት ነገር ምስጋና ማቅረብ አይደለምን ?
አዎ! በተሳሳተ አመለካከት እየተነሱ ሲተኩሱበት መሣሪያውን የሚዘቀዝቅ ህዝብ አክባሪ የሆነውን ሠራዊት ማክበር ታላቅነት ነው፣ የራሱን ስንቅ ለህዝብ የሚያድል የሀገር እና የህዝብ አለኝታ የአንድነታችን አርአያ የሆነውን ሠራዊት ማክበር፣ መደገፍ ፣ከጎኑ መቆም ሀገርን ከመውደድ ባሻገር መታደልም ነው።
የኢትዮጵያን አንድነት እያሥጠበቀ ሀገርን ለትውልድ እያሸጋገረ የሚገኘውን መከላከያ ሠራዊት ማክበር ክብር መሥጠት ማመስገን እና ሁሌም ከጎኑ መሠለፍ ተገቢም አማራጭም ነው።
ለዛም ነው መከላከያ ሠራዊቱን መውደድ መከላከያ ሠራዊቱን ማክበር ሀገርን መውደድ ሀገርን ማክበር ነው የምንለው።
በውብሸት ቸኮል
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official