በኢትዮጵያ የተገነባው ዘመናዊና ጠንካራ ሰራዊት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት በአስተማማኝ መልኩ የሚጠብቅ ነው – ጄኔራል አበባው ታደሰ

በኢትዮጵያ የተገነባው ዘመናዊና ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት በአስተማማኝ መልኩ የሚጠብቅ መሆኑን የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ገለጹ።

የደቡብ ዕዝ 21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ሌሎችም ታዳሚዎች በተገኙበት ተከብሯል።

በዚሁ ሁነት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር  ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፤የሀገር መከላከያ ሰራዊት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣በብቃትና ጀግንነቱ ጭምር የኢትዮጵያ አስተማማኝ አለኝታ መሆኑን ገልጸዋል።

የውስጥ ባንዳዎችንና የውጭ ጠላቶችን ከንቱ ህልሞች በማምከን ኢትዮጵያ ተከብራና ሉአላዊነቷ ተከብሮ እንድትዘልቅ ያደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

በኢትዮጵያ የተገነባው ዘመናዊና ጠንካራ ሰራዊት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት በአስተማማኝ መልኩ የሚጠብቅ ነው ሲሉም አረጋግጠዋል።

የደቡብ ዕዝ 21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ባለፉት 30 ዓመታት ሰላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ ባለፈ በርካታ  ወታደራዊ መሪ ያፈራና ትምህርታዊ ልምድ የተወሰደበት  የሰራዊት ክፍል መሆኑንም አንስተዋል።

የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ፥ ክፍለ ጦሩ የፀረ ሰላም ሃይሎችን የሽብር እንቅስቃሴ በማክሸፍ  አኩሪ ገድል በመፈፀም  ሀገርን  በማፅናት በኩል የላቀ ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ክፍለ ጦሩ የተለያዩ ክፍለ ጦሮች እንዲመሰረቱ ልምድና መሰረት በመሆን እያገለገለ መሆኑንም ተናግረዋል።

የባቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመዲን እስማኤል ፤ የከተማዋና አከባቢዋ ሕብረተሰብ የኢትዮጵያ ጠንካሬ መገለጫ ከሆነው የሀገር መከላከያ ጎን ነው ብለዋል።

የአካባቢው ሕብረተሰብ ሰላምን በማፅናት ልማትና ዕድገት በተሻለ ደረጃ እያስቀጠለ ነው ያሉት ከንቲባው፥ባቱና የአካባቢዋ ማህበረሰብ ሰላሙን በመጠበቅ ረገድ ከሀገር መከላከያና ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር በመስራት ሰላምን በማረጋገጥ የበኩላቸውን እንደተወጡ ገልጸዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው በክበረ በዓሉ ላይ የሀገር ህልውና በማስጠበቅ ላይ ለተሰውና በክብር ለተሰናበቱ  የክፍለ ጦሩ አባላት ቤተሰቦች እውቅና ተሰጥቷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

FDRE Defense Force – የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት, [10/7/2025 3:53 PM]

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2025-10-08_21-49-49
ከጀግኖች አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር በጀግንነት ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
photo_2025-10-08_16-00-00
የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሠራዊቱን ዝግጁነት ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው።   አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም
photo_2025-10-08_21-36-23
የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት በላቀ ብቃትና ዝግጁነት የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -   ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ
photo_2025-10-06_09-06-37
ለምስራቅ ጉጂ ዞን ሠላም አሥተዋፅኦ ላበረከተው ኮር ዞኑ ምስጋና አቀረበ።
photo_2025-09-23_22-13-45
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሠራዊቱን አቅም እየገነባ ይገኛል።     ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2025-09-23_17-24-05
ሴቶች በሁሉም መስክ ፊት በመሠለፍ ውጤታማ ተግባራት ማከናወን እንዳለባቸው ተገለፀ።

ስፖርት

photo_2025-10-08_21-49-49
ከጀግኖች አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር በጀግንነት ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
photo_2025-10-08_16-00-00
የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሠራዊቱን ዝግጁነት ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው።   አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም
photo_2025-10-08_21-36-23
የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት በላቀ ብቃትና ዝግጁነት የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -   ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ
photo_2025-10-06_09-06-37
ለምስራቅ ጉጂ ዞን ሠላም አሥተዋፅኦ ላበረከተው ኮር ዞኑ ምስጋና አቀረበ።
photo_2025-09-23_22-13-45
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሠራዊቱን አቅም እየገነባ ይገኛል።     ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2025-09-23_17-24-05
ሴቶች በሁሉም መስክ ፊት በመሠለፍ ውጤታማ ተግባራት ማከናወን እንዳለባቸው ተገለፀ።

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ