ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ የሳምባ ምች መንስኤዎች

የሳምባ ምች የሚከሰተው በባክቴሪያ፣ ቫይረስ ወይም ፈንገስ ምክንያት ሳምባ ላይ በሚፈጠር ኢንፌክሽን ነው። የሳምባ ምች ቀዳሚ መንስኤዎች የባክቴሪያ እና የቫይረስ ኢንፌክሽን ናቸው።

በትንፋሽ ወቅት የሳምባ ምች የሚፈጥሩ ጀርሞች አልቪዮሊ ተብለው የሚጠሩ ትናንሽ ከረጢቶች ውስጥ ገብተው ይባዛሉ።

ባክቴሪያ እና ቫይረሶች የሳንባ ከረጢቶችን በፈሳሽ እንዲሞላ በማድረግ የሳምባ ምች እንዲፈጠር ያደርጋሉ።

የሳምባ ምች በወጣት እድሜ ላይ ባሉ ጤነኛ ሰዎች ላይ ይፈጠራል። ነገር ግን በሽታው በአዛውንት፣ በህፃናት እና የሌላ በሽታ ታካሚዎች ላይ በይበልጥ ይከሰታል።

የበሽታዉ ምልክቶች ሳል ፤ትኩሳት ፤ትንፋሽ ማጠር የሚያንቀጠቅጥ የብርድ ስሜት፤ የደረት ህመም ፤ፈጣን የልብ ምት ፤የድካም ስሜት ፤የማቅለሽለሽ ስሜት ፤ማስመለስ ፤ራስ ምታት ፤የጡንቻ ህመም የመሳሰሉት ናቸው።

የበሽታው መከላከያ መንገዶች በሳምባ ምች ከተጠቃው ሰው በሳል፣ በማስነጠስ እና ተመሳሳይ ቁሶች በጋራ በመጠቀም ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። የባክቴሪያ ሳምባ ምችን ለመከላከል ክትባቶችን መከተብ ከተለያዩ የምች ኢንፌክሽኖች ስለሚከላከሉ ለልጆችም ሆነ ለአዋቂዎች የሚመከሩ ናቸው።

ለመከላከል በተጨማሪ መደረግ የሚገባቸው አዘውትሮ እጅን መታጠብ ፤ሲያስነጥሱ ወይም ሲያስሉ አፍን መሸፈን ፤ አለማጨስ ፤ የተመጣጠነ ምግብ መብላት ፤የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፤ የሳምባ ምች በሽታ ካለባቸው ሰዎች ሳል እና አክታ መራቅ ናቸው።

የበሽታው ህክምና እንደ አይነቱ እና ክብደቱ ይወሰናል የባክቴሪያ ምች በአንቲባዮቲክ ይታከማል፤ የቫይረስ ምች እረፍት በመውሰድ እና በቂ ፈሳሽ በመውሰድ ይታከማል፤ የፈንገስ ምች በጸረ-ፈንገስ መድሃኒቶች ይታከማል የሳምባ ምች ምልክቶችን ለማከም የተለያዩ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ፦

ለትኩሳት፣ ለሳል እና ለህመም የሚሆኑ ፡፡ በቂ እረፍት መውሰድ ፤በቂ ፈሳሽ መውሰድ ፤ምልክቶቹ ከተባባሱ ወይም የታካሚው በሽታ መከላከል አቅም ከወረደ ሆስፒታል መተኛት ሊያስፈልግ ይችላል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-10-27_02-32-52
ኢትዮጵያ እና ኳታር በወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፡፡
photo_2026-10-25_07-18-37
ለህወሃት አምስተኛ ዕድል አንሰጠውም - ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2026-10-25_07-35-07
መከላከያ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የህዳሴ ጉዞና ዘላቂ ሰላም የሚያስጠብቅ ዋስትናችን ነው::  አቶ መሃመድ እድሪስ
photo_2026-10-25_07-53-26
የኢትዮጵያ የታጠቀ ኃይል በየዘመናቱ ታሪክ እየሠራ ያለፈ ነው:: ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ
photo_2026-10-25_08-18-34
ለትውልድ የሚሸጋገር ታሪክ እየሰራን መጓዛችንን እንቀጥላለን።    ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
photo_2026-10-25_08-24-55
የኢትዮጵያ ሠራዊት አይበገሬነቱን በተግባር የሚሳይ አስተማማኝ የድል ሠራዊት ነው። ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ

ስፖርት

photo_2026-10-27_02-32-52
ኢትዮጵያ እና ኳታር በወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፡፡
photo_2026-10-25_07-18-37
ለህወሃት አምስተኛ ዕድል አንሰጠውም - ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2026-10-25_07-35-07
መከላከያ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የህዳሴ ጉዞና ዘላቂ ሰላም የሚያስጠብቅ ዋስትናችን ነው::  አቶ መሃመድ እድሪስ
photo_2026-10-25_07-53-26
የኢትዮጵያ የታጠቀ ኃይል በየዘመናቱ ታሪክ እየሠራ ያለፈ ነው:: ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ
photo_2026-10-25_08-18-34
ለትውልድ የሚሸጋገር ታሪክ እየሰራን መጓዛችንን እንቀጥላለን።    ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
photo_2026-10-25_08-24-55
የኢትዮጵያ ሠራዊት አይበገሬነቱን በተግባር የሚሳይ አስተማማኝ የድል ሠራዊት ነው። ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።