የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሰይድ ሙባረክ ሰይድ አሊ ጃፋር አልሚኖ ጋር በፅህፈት ቤታቸው የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡
ሚኒስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ ኳታር በቅርብ ጊዜ በሽብር ኃይሎች ጥምረት የሀገርን እና የኢትዮጵያን ህዝብ ሰላም ለማደፍረስ አላማ ያደረገውን ጦርነት አስመልክቶ የሰጠችው ፍትሃዊ እና ጠንካራ መግለጫ ሀገሪቱ ከእውነት ጎን ለመቆም ያላትን ቁርጠኝነት ያመላከተ መሆኑን በመግለፅ አመሰግነዋል።

በቀጣይም በሀሉቱ ሀገራት መካከል የሚደረገውን ወታደራዊ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር መስራት እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡
አምባሳደር ሰይድ ሙባረክ ሰይድ አሊ ጃፋር አልሚኖ በበኩላቸው ወይይቱ ከአዲሱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ከአቶ መሀመድ እድሪስ ጋር ለመተዋወቅ እና በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት ወታደራዊ እና ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በር እንደከፈተላቸው ገልፀዋል።
በቀጠናዊ እና በዓለምአቀፋዊ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለቱንም ሀገራት ክብር እና ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የሚችሉ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትብብሮችን ለማድረግ ጠቃሚ ውይይት በማደረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
