ጉብኝቱ በወታደራዊ ሙዝየም ዘርፍ የልምድ እና የተሞክሮ ልውውጥ ማድረግን አላማው ያደረገ ሲሆን ኤክስፐርቶቹ አጠቃላይ የሙዚየሙን አሁናዊ ሁኔታ እና ቀጣይ ሊገነባ ስለታቀደው ዘመናዊ ወታደራዊ ሙዚየም ሰፋ ያለ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ጎብኚዎቹ በበኩላቸው በኒጀር ሊገነባ ስለታሰበው ወታደራዊ ሙዚየም ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ጉብኝቱም ቀጣይ ለሚሰሩት ስራ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆንላቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየም የወታደራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጽሐፍት መምሪያ ሀላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ ታደሰ ጎብኚዎቹ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ጠቁመው ቀጣይ በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ላይም መወያየታቸውን ተናግረዋል።
ጉብኝቱ ስለ ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ታሪክ የነበራቸውን ግንዛቤ እንዳሰፋው የገለጹት የኤክፐርት ቡድኑ መሪው ሲንየር ኮሎኔል ሀምዱ ድጂቦ በኒጀር ለሚገነባው ወታደራዊ ሙዚየም ስራም ትልቅ ልምድ እና ተሞክሮን መቅሰማቸውን ጠቁመው ቀጣይ ከሙዚየሙ ጋር በርካታ ስራዎችን በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
