ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሁርሶ የወሰዱት ሥልጠና የአመራርነት ብቃትን እንደሚያሳድግ ገለፁ።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሁርሶ ዕጩ መኮንኖች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት የወሰዱት የወታደራዊ ሳይንስ ሥልጠና የአመራርነት ብቃትን ለማሳደግ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

ዶክተር ጌዲዮን ስልጠናው ወታደራዊ ሳይንስን በተግባር ለመረዳት፣ የመከላከያ ሠራዊቱን የሥራ ሂደትና የስልጠና ሥርዓት በቅርበት ለመገንዘብ እንዲሁም በአካላዊ፣ በአእምሯዊና በተግባር ዝግጁነት ረገድ አዲስ አቅም ለመጨበጥ እንዳስቻላቸውም ገልፀዋል።

በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ አስተማማኝ የመከላከያ አደረጃጀትና አወቃቀር እንድትገነባ የወታደራዊ ሳይንስ ጥበብን ማወቅ አሥፈላጊ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ ያገኙት ተሞክሮ የወታደራዊ ሳይንስን ፋይዳ በተግባር ከመረዳት ባለፈ፣ በአመራር ሥራቸው የተሻለ ግንዛቤና ዝግጁነት እንዲኖራቸው የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ የወታደራዊ ሳይንስ ስልጠና ለሲቪል አመራሮቹ ስለወታደራዊ አስተሳሰብ፣ስለ መከላከያ ስርዓት፣ ስለ ሃገራዊ ደህንነትና ስለ ስትራቴጂካዊ ውሳኔ አሰጣጥ ያላቸውን ግንዛቤ ለማስፋት ጠቃሚ መሰረት መፍጠሩን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣አመራሮቹ የሃገርን ደህንነት የስጋት ምንጮችንና የብሄራዊ ጥቅም ጉዳዮች በሰፊው እንዲገነዘቡ ያስቻለ ሥልጠና ሥለመሆኑም አንስተዋል።

ከፍተኛ አመራሮች የወታደራዊ ሳይንስ ስልጠና ከሚያበረክታቸው ጠቀሜታዎች መካከል የተግባቦት ክፍተትን ማጥበብ፣ የጋራ ግንዛቤን ማሳደግ፣የውሳኔ አሰጣጥን ማሻሻልና በተቋማት መካከል የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት አቅምን እንደሚያጠናክር ገልፀዋል።

በተለይም የሃገር ደህንነትን የሚፈትኑ ውስብስብ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በቂ ዕውቀት ያላቸው አመራሮች ሁኔታዎችን በተሻለ ሁኔታ እንዲተነትኑ አማራጮችን እንዲመዝኑና የሃገርን ዘላቂ ጥቅም የሚያስጠብቁ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ ሥልጠናው ጠቃሚ መሆኑን ከፍተኛ አመራሮች ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ አጀንዳ

do
ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሁርሶ የወሰዱት ሥልጠና የአመራርነት ብቃትን እንደሚያሳድግ ገለፁ።
photo_2026-11-06_03-25-50
የኒጀር ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየምን ጎበኙ።
y
የፖለቲካ አመራሮች የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ስልጠና መውሰዳቸው የአመራር ብቃትን ያጎለብታል።       ጄኔራል ይመር መኮነን
f
ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ታሪካዊ ግንኙነታቸውንና ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ
ko
ኢትዮጵያ ለኮሪያ የከፈለችው መስዋዕትነት በኮሪያ ህዝብ ዘንድ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል፦   ሜጀር ጄኔራል ሊ ው ሄዎን
b1
6ኛ ዓመት ሰሜን ዕዝ መታሰቢያ በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ታስቧል።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።