የጦር ኃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያሰለጠናቸውን የጤና ሙያተኞች አስመረቀ።

በመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የጦር ኃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በፊልድ ሰርጀሪ፣ በረዳት አንስቴዥያ እና በኦፕሬሽን ሩም (OR) ነርሲንግ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን የጤና ባለሙያዎችን አስመርቋል።
‎
‎በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት የሥራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ተወካይ ብርጋዲየር ጀነራል የሺእመቤት አያሌው  የጤና ባለሙያዎችን ብቃት ታታሪነትና የሥራ ኃላፊነት ስሜት ማሳደግ ለሠራዊቱ የጤና አገልግሎት ጥራት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

ተመራቂዎቹም በሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በተግባር በማዋል ለሠራዊቱ ጤና መረጋገጥ በቁርጠኝነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።
‎
‎የወታደር ጤና መጠበቅ የግለሰብን ሕይወት ከመታደግ ባሻገር፣ የሠራዊቱን የሥራ ብቃት፣ የተልዕኮ አፈጻጸምና ወታደራዊ ዝግጁነት ለማስጠበቅ ያስችላል ያሉት ጀነራል መኮንኗ ሠራዊቱ በተለያዩ ሁኔታዎች የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣ ከሚያግዙ መሠረታዊ ጉዳዮች ዋናው ጤና መሆኑን አስገንዝበዋል።
‎
‎የጦር ኃይሎች ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኃላፊ ተወካይ ብርጋዲየር ጀኔራል ዶክተር ገነት ይማም፣ በሠራዊቱ የጤና ሥርዓት ውስጥ የዳበረ አቅም ያለው ሙያተኛ አስፈላጊ በመሆኑ የዛሬ ተመራቂዎችም ይህንኑ መሠረት ያደረገ እና የተቋሙን ክፍተት የሚሞሉ ናቸው ብለዋል።

ሰልጣኞች የቀዶ ሕክምናና የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ ሙያዊ አቅም የሚፈጥሩ ስለመሆኑን አብራርተዋል። የፊልድ ሰርጀሪ ሙያ በጦር ሜዳና በሌሎች አስቸኳይ ሁኔታዎች ውስጥ የሚደርሱ የአካል ጉዳቶችን በፍጥነት ለማከምና ወቅታዊ የቀዶ ሕክምና ድጋፍ ለመስጠት ያግዛል ብለዋል።
‎

ወቅታዊ አጀንዳ

a
ኢትዮጵያና አሜሪካ ታሪካዊ ግንኙነታቸውን እና ቀጠናዊ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።
g
የመከላከያ ሚኒስትሩ MNS ጋርመንት ኢንዱስትሪን ጎበኙ።
b
በሴራና በተንኮል የባህር በር እንድናጣና የባህር ኃይላችን እንዲፈርስ መደረጉ ሀገራችንን ለተለያዩ ተግዳሮቶች ዳርጓታል።         ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ
se
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ወታደራዊ ዝግጁነት አረጋገጠ፡፡
te
የጦር ኃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያሰለጠናቸውን የጤና ሙያተኞች አስመረቀ።
do
ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሁርሶ የወሰዱት ሥልጠና የአመራርነት ብቃትን እንደሚያሳድግ ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።