የመከላከያ ሚኒስትሩ MNS ጋርመንት ኢንዱስትሪን ጎበኙ።

የመከላከያ ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ የተቋማትን የሥራ እንቅስቃሴ ጉብኝታቸውን በመቀጠል፣ በመከላከያ ፋውንዴሽን ስር የሚተዳደረውን MNS ጋርመንት ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት በፋብሪካው የምርት ሂደት ላይ በተመለከቱት መደሰታቸውን ገልፀው፤ ፋብሪካው ዲጂታላይዜሽንን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለማላመድ ያደረገውን ጥረት እንደማሳያ በመጠቀም ፋብሪካው ከውጭ አካል ድጋፍ ከመጠበቅ ይልቅ፣ በራሱ አቅም እና በፈጠራ መንፈስ የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሄደበትን ርቀትን አድንቀዋል።

ለዚህ ለተቋሙ እድገት ጠንካራ ድጋፍ ላደረገው ለስትራቴጂካዊ አመራሩ ምስጋና አቅርበው፣ በቀጣይም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ (Quality Assurance) እንዲያሟላና ከቴክስታይል ማኅበራት ጋር በመቀራረብ የገበያ ትስስር ችግሮችን በዘላቂነት እንዲቀርፍ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

MNS ጋርመንትና ቴክስታይል ፋብሪካ ከፈትል እስከ መሸመን ባለው ሙሉ አደረጃጀት የሚታወቅ ሲሆን፤ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አልባሳትን በማቅረብ፣ እንዲሁም ከጥጥ የተሰሩ የቤት ውስጥ ጨርቃጨርቅና የደንብ አልባሳትን ለልዩ ልዩ ተቋማት በማቅረብ በሀገር ውስጥ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል። ዘገባውን ያደረሰን የሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ነው

ወቅታዊ አጀንዳ

a
ኢትዮጵያና አሜሪካ ታሪካዊ ግንኙነታቸውን እና ቀጠናዊ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።
g
የመከላከያ ሚኒስትሩ MNS ጋርመንት ኢንዱስትሪን ጎበኙ።
b
በሴራና በተንኮል የባህር በር እንድናጣና የባህር ኃይላችን እንዲፈርስ መደረጉ ሀገራችንን ለተለያዩ ተግዳሮቶች ዳርጓታል።         ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ
se
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ወታደራዊ ዝግጁነት አረጋገጠ፡፡
te
የጦር ኃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያሰለጠናቸውን የጤና ሙያተኞች አስመረቀ።
do
ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሁርሶ የወሰዱት ሥልጠና የአመራርነት ብቃትን እንደሚያሳድግ ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።