የኢንስፔክሽን ቡድኑ የሠላም አሥከባሪውን ሻለቃ የዝግጁነት ሁኔታ አረጋግጧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

በአትሚስ የሴክተር 3 ኢንስፔክሽን ኃላፊ አቶ ጀምስ ነካሻ የ2024 የመጀመሪውን ሩብ ዓመት የሰራዊቱን ዝግጁነት ለማረጋገጥ በተደረገው ኢንስፔክሽን ሠላም አሥከባሪ ሻለቃው በጥሩ አቋም ላይ እንደሚገኝ አረጋግጧል።

ከጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመስራቴ ደስተኛ ነኝ ኢትዮጵያዊያን መዋጋት ጠላትን ማንበርከክና ማሽነፍ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ በአትሚስ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ የተሳካ እንዲሆን ለሱማሊያ ህብረተሰብ መስዋዕትነት እየከፈሉ የሚገኙ ናቸው ሲሉ መሥክረዋል።

ሠራዊቱ ለተልዕኮ ስኬት ቅድሚያ በመስጠት ንብረቶቹ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የረጃም ጊዜ እንክብካቤና ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ማሳያ ነው ተልዕኮውን ለመወጣት የሚረዳውን ንብረቶች በመንከባከብም አርአያ ነው ብለዋል።

የሴክተር 3 ሰላም ማስከበር ኢንስፔክሽን ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ግርማ ሽብሩ ሁሉም የሴክተሩ አባላት በተሰማሩበት በባይድዋ፣ በቡራካባ፣ በባርደሬ፣ በገብርሃሬ፣ በዲንሱር፣ በባርደሌ፣ በቡርዱቦና በቀንሳ ሃደሬ አካባቢዎች የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ ሻለቃ ዝግጁነት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

የሴክተር 3 ጥገና ኃላፊ ሻምበል መንግስቱ ማቲዎስ በክፍላችን የሚገኙት ሞያተኞች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እንደ ወታደር የአትሚስን አህጉራዊ ተልዕኮ ለመፈፀም መንግስትና ህዝብ የሰጠንን አደራ እየተወጣን የተበላሹ ተሸከርካሪዎችንና ማሽነሪዎችን በመጠገን ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ ሠመረ እሸቱ

ፎቶግራፍ ከሻለቆች

ወቅታዊ አጀንዳ

mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።
F
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
A1
አንድ ሆነን በአድዋ እንዳስመዘገበነው ድል በጋራ ሆነን የአክሲዮን ማህበራችንን ስኬት እናረጋግጥ፦    ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
P
በሶማሊያ ሴክተር 3 የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የ18 ወራት ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ