የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
በዕለቱ በክብር እንግድነት ተገኝተው ማዕረግ በማልበስ የስራ መመሪያ የሠጡት የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ ፤ ማዕረግ የመቆያ ጊዜን ብቻ በመሸፈን የሚሠጥ ሳይሆን ሀገር፣ ህዝብና መንግስት የሰጣችሁን ሃላፊነት እና ተልዕኮ በሚገባ በመወጣት የሚሰጥና የበለጠ የስራ ተነሳሽነት የሚፈጥር የድካማችሁ ውጤት ነው ብለዋል።
ተሿሚዎች ትናንት እየተወጣችሁ ለመጣችሁት የስራ ትጋት ተቋሙም ሆነ መንግስት ትልቅ ክብርና አደራ እየጣሉባችሁ እንዳለ ተገንዝባችሁ ለበለጠ ስራ እና ሃላፊነት ራሳችሁን ማዘጋጀት ይጠበቅባችሁል ሲሉ አሳስበዋል ዘገባው የጋብዘው ዳና ነው።
በተያያዘም የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ለከፍተኛ መኮንኖች ፤መስመራዊ መኮንኖች እና ለባለሌላ ማእረግተኞች ማዕረግ አልብሷል።
ሹመቱ የተሰጠው የማዕረግ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ ሲሆን ያላቸው ልምድ አና ብቃት ተገናዝቦ ወደ ቀጣይ ማዕረግ የሚሾሙበት ቦታ መኖሩ ተረጋግጦ መሆኑን የዋና ዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ ደመቀ መናገራቸውን ያደረሠን ፅህፈት ቤቱ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ