የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ክፍለጦር አመራሮች እና አባላት ደም ለገሱ፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ሞ
የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ክፍለጦር የሰራዊት አባላት እና አመራሮች በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው ደም ልገሳ መርሃ ግብር ላይ አንድም ኢትዮጵያዊ በደም እጥረት ምክንያት መሞት የለበትም በሚል መሪ ቃል በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በሚገኘዉ ሆስፒታል ደም ለግሰዋል፡፡
የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የኮማንዶ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ነፃነት ሠራዊቱ የህዝብን ህይወት ለመጠበቅ ግዳጆችን መወጣቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ህዝባችን የእኛን እርዳታ እና እገዛ በሚፈልገበት ከጎኑ በመቆም አለኝታነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ዘጋቢ ሳላምላክ በላይ
ፎቶ ግራፍ ፍሬው ፈጠነ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official