የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 06 ቀን 2017 ዓ.ም
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ አንድ ክፍለ ጦር በአሸባሪው የሸኔ ቡድን ላይ እርምጃ መውሰዱን መቶ አለቃ አለልኝ ፀሃዬ ተናግረዋል። በጥፋት ቡድኑ ላይ በተወሠደ እርምጃ ህዝብ ሲያግትና ሲዘርፍ የነበረውን ቡድን መምታት መቻሉንም ገልፀዋል።
የተወሰደው እርምጃ ለህብረተሰቡ ጥሩ እፎይታን የሚፈጥር መሆኑን የገለፁት መቶ አለቃ አለልኝ ሠራዊቱ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ህብረተሠቡ አሥፈላጊውን ጥቆማ በመሥጠት እና የሸኔ ቡድን እንዲመታ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ አሥተዋፅኦ እያደረገ ሥለመሆኑም አሥረድተዋል።
መቶአለቃ አለልኝ በሠላም እጁን የሚሠጥ ሸኔን ሠራዊቱ በእንክብካቤ እንደሚይዝ ገልፀው እጁን ለመሥጠት ዝግጁ ያልሆነውን ግን አድኖ የመምታት ሥራውን እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
ዘጋቢ አለባቸው ዳኜ
ፎቶ ግራፍ ሲሳይ ነጋሽ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ