ለምረቃ የበቁ የመሠረታዊ ኮማንዶ ሰልጣኝ አባላቱ የቁርጠኝነት ማሳያ ስለመሆናቸው ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም.

የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል መሠረታዊ ኮማንዶዎችን አሰልጥኖ ለ43 ጊዜ አስመርቋል።

ካራማራ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው የመሠረታዊ ኮማንዶ ሰልጣኝ አባላቱ የተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችን በማሳየት ብቃታቸውንም አረጋግጠዋል።

የ43ኛው ዙር የኮማንዶ ሰልጣኞች ምረቃ ስነስርዓት የሰልጣኞቹ ጥንካሬና ብቃት ጎልቶ መታየቱን የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄነራል ሹማ አብደታ ተናግረዋል።

ሌተናል ጄነራል ሹማ አብደታ ሰልጣኞቹ የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ውስብስብ ግዳጅ እንኳን ቢሆን ሊዋጡ የሚችሉ የውጊያ ማርሽ ቀያሪ የልዩ ሀይል አባላት ማፍራታቸውን ተናግረዋል።

አዛዡ አክለውም ማሰልጠኛው የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይሉን የሚያጠናክሩ ለቀጣይም ሀገራዊ ተልዕኮ ዝግጁ የሆኑ የልዩ ዘመቻዎች ሀይል የማጠናከርና የማፍራት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ተመራቂ አባላቱ የቀይ መለዮ አለባበስ ስነ ስርዓቱም በጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የለበሱ ሲሆን ሀገራቸውን በቅንነት ለማገልገል ያላቸውን ቁርጠኝነት በቃለ-መሀላ አረጋግጠዋል።

በራሔል ገዛኸኝ

ወቅታዊ አጀንዳ

mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።
F
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
A1
አንድ ሆነን በአድዋ እንዳስመዘገበነው ድል በጋራ ሆነን የአክሲዮን ማህበራችንን ስኬት እናረጋግጥ፦    ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
P
በሶማሊያ ሴክተር 3 የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የ18 ወራት ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ