ኮሌጆች እና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች የተቋሙን ዝግጁነት የሚያጠናክር ውጤታማ ስራዎችን ሠርተዋል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የበጀት ዓመቱን የስራ አፈፃፀም ውይይት አድርጓል። በውይይቱ በዋና መምሪያው ስር ያሉ ኮሌጆችና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች የተገኙ ሲሆን የስራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን በማቅረብ በጠንካራ እና በእጥረቶች የታዩ አፈፃፀሞች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ከውይይቱ በኋላ በአዲሱ 2018 በጀት ዓመት እንደ መከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሊተገበሩ የታቀዱ ዕቅዶች ላይ በዝርዝር ውይይት የስራ መመሪያ እንደሚሰጥ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንን አመላክተዋል።
በዛሬ ውሎው በቀረበው የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በሁሉም ኮሌጆች እና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች የተቋሙን ዝግጁነት በማጠናከር በርካታ ውጤታማ ስራዎች እንደተሰሩ ተገልጿል።
በተቋሙ ኮሌጆችና ማሰልጠኛ ተቋማት ቁጥራቸው ከመቶ በላይ የሆኑ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ወታደራዊ አመራሮች ሰልጥነው መመረቃቸው በወታደራዊ ዲፕሎማሲው መስክ እና በሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ዲፕሎማሲ እንደሚያጠናክር ተገልጿል።
ዘጋቢ አባቱ ወልደማሪያም
ፎቶግራፍ አበረ አየነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
http://localhost/defensenew/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official