የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሶማሊያ ህዝብ ውድ ህይወቱን ከፍሏል ህዝባዊነቱንም አሳይቷል።

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ከልል መንግስት የሴክተር 3 ዋና አዛዥ ሆነው ለቆዩት ብርጋዲየር ጀኔራል በስፋት ፈንቴ እና ለአዲሱ የሴክተር 3 ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ተክሉ ሁሬሳ የአሸኛኘትና የአቀባበል ሥነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የሃገር ሽማግሌዎችን በመወከል መላቅ መሃመድ ያቁብ ሼክ ዴሮው፣የክልሉን ሚኒስትሮች በመወከል  የደቡብ ምዕራብ ሱማሊያ ኢንቨስትመንት እና ዕቅድ ሚኒስትር አቶ አብድሃኪም መሀመድ ሃጂ ፊቅ፣የባይድዋ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱላሂ ወቲን፣የባይ ዞን አስተዳደር አቶ አሊ ወርዴር ዶዮው የክልሉን መንግስት ወክለው ዕውቅናና ሽልማት አበርክተዋል።

ተወካዮቹ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሶማሊያ ህዝብ ለረጅም አመታት ውድ ህይወቱን የከፈለ አስካሁንም ድረስ ህዝባዊነቱ፣የግዳጅ አፈፃፀሙ በሶማሊያ ህዝብ የተመሰከረለትና በህዝብ ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንዲደርስ የማይፈቅድ ቀጠናችንን ከመጠበቅና ሰላምን ከማረጋገጥ ባለፈ የተቸገሩትን በምግብ፣ በአልባሳት፣ በህክምናና በተለያዩ አገልግሎቶች ከኪስ ገንዘቡ በማዋጣት የሚረዳ የሚመሠገን ሠራዊት ነው ብለዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኤዩሶም ቺፍ ኦፍ ስታፍ ሜጀር ጀኔራል ክንዱ ገዙ የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ህዝብና መንግስት ላዘጋጃችሁት ደማቅ አቀባበልና ሽኝት ስነ-ስርዓት በኢትዮጵያ መከላከያሠራዊትና ኤዩሶም ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ለሠራዊታችንና ለሴክተሩ አመራሮች ያላችሁ ክብር ታላቅ እንደሆነ መረዳታቸውን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ ይህ ታላቅ ክብር ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን የደቡብ ምዕራብ ሱማሊያ ህዝብና መንግስት ትላንት በአስቸጋሪ ወቅትም በአደባባይ ወጥቶ ኢትዮጵያዊያን የከፈሉትን ዋጋ እውቅና የሰጠን ህዝብና መንግስት ነው ብለዋል፡ቀጣይም ያለንን ግንኙነት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

ዘጋቢ ሰመረ እሸቱ

ፎቶግራፍ አይናለም ተክለፃዲቅ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ
m
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከሪፖርታጅ ፕሮፐርቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረመ።
j
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፦    ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።