በአድዋ ድል መታሰቢያ በፀጥታና ደህንነት ተቋማት የተዘጋጀ ጷጉሜን 01 የጽናት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ መክፈቻ ለይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትርና የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ፅናት የታሪካችን አካል ፣የኑሯችን ዘይቤ ለትውልዱ የምናወርሰው አኩሪ ዕሴታችን ነው ብለዋል።
በዓሉ ሲከበር በፅናት ሀገራቸውን ላገለገሉ ክብር የሚሰጥበት ፣ ያለንን የፅናት ጥንካሬ የምናስቀጥልበትና ለመጭው ትውልድ የምናወርስበት መሆኑን ገልፀዋል።

ቀኑን ስናከብር የኢትዮጵያ መልክ የሆነውን ፅናት ተላብሰን ያስመዘገብናቸውን ድሎች ለማስቀጠልና የሚገጥሙ ፈተናዎችን ወደ መልካም ዕድል በመለወጥ ሀገራችንን ወደ አዲስ ብሩህ ተስፋ ለማሸጋገር የምንሰራበትም ሊሆን ይገባል ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
በዝግጅቱ ላይ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰን ጨምሮ የቀድሞ የሀገራችን ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ሚኒስትሮች ፣የፀጥታና ደህንነት ተቋማት አመራሮች የስራ ሀላፊዎች፣ ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊቱና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ በፀጥታ ተቋማቱ የተዘጋጀ የዲጅታል ኢግዚቢሽን ቀርቧል።
ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official