ኢትዮጵያ በርካታ ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ ያላት ሃገር ናት። ብርጋዲየር ጄኔራል ረዛቅ አህመድ።

በደቡብ ሱዳን የሴክተር ኢስት አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ራዛቅ አህመድ የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በደቡብ ሱዳን ቦር ከሚገኘው የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ጋር አክብረዋል።

‎ብርጋዲየር ጀነራል ራዛቅ አህመድ፤ ኢትዮጵያ ከአለም ሃገራት ከምትለይባቸው በርካታ ዘመን ተሻጋሪ አኩሪ  ታሪኮቿ ውስጥ የሰው ዘር መገኛና የራሷ የዘመን አቆጣጠር ቀመር እንዲሁም ፊደልን ቀርፃ መጠቀሟ  ነው ብለዋል።

‎ኢትዮጵያ አስደናቂ ባህል ያላት ድንቅ ምድር መሆኗን የጠቀሱት ብርጋዲየር ጀነራል ራዛቅ አህመድ በተለይ በሰራዊቱ ውስጥ የሚታየው የራስንም የሌሎችንም ባህል የማክበር ጥሩ ስነ-ምግባርን አጠናክሮ ከማስቀጠል ባሻገር  እንደ ወታደር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በውስጣቸው ያለው ጓዳዊነት ከራስ ባለፈ ለሌሎች ሃገራት ሰራዊቶች አርአያ መሆን የሚችል ነው ብለዋል።

‎አዲሱን  የዘመን መለወጫ በዓል ስታከብሩ ከዩናሚስ የተሰጣችሁን ዋነኛ ተልዕኮ በጀመራችሁት በተግባር እየታየ ባለው ውጤት ልክ አጠናክራችሁ በመቀጠል በተለይ የሰላም ግንባታ ላይ ዩናሚስ በቀጠናው እንዲመጣ በሚፈለገው ልክ ለመስራት መትጋት ይኖርባችኋል በማለት አሳስበዋል።

‎የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በአለም ሰላም ማስከበር ሂደት ውስጥ  ያለውን ለዘመናት የቆየ ስምና ዝናን አስጠብቀን ለመቆየትና ለአለም ሰላም ባለን ቁርጠኝነት ልክ በአዲሱ ዘመን በተሻለ ውጤት የነበረውን ውጤት ለማስቀጠል እንሰራለን በማለት ተናግረዋል።

‎ዘጋቢ አንዋር ሁሴን
ፎቶ ግራፍ መብርሂት ገብረሚካኢል

ወቅታዊ አጀንዳ

mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።
F
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
A1
አንድ ሆነን በአድዋ እንዳስመዘገበነው ድል በጋራ ሆነን የአክሲዮን ማህበራችንን ስኬት እናረጋግጥ፦    ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
P
በሶማሊያ ሴክተር 3 የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የ18 ወራት ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ