የሀገራችን ሰላም እና ልማት የተረጋገጠው በፀጥታ ኃይሎቻችን ፅናት እና መስዋዕትነት ነው አቶ አወል አርባ

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የሠራዊት አባላት የፅናት ቀንን “ፅኑ መሰረት ብርቱ ሀገር  ” በሚል መሪ ቃል ከሰመራ ከተማ ነዋሪዎች ፣ ከክልል እና ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር በጋራ አክብረዋል።

በስነ- ስርዓቱ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አወል አርባ ፣ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮል እና የአፋር ክልል ሲቪል አመራሮች እንዲሁም የፀጥታ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ርዕሰ -መስተዳድሩ በስነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የኢፊዴሪ መከላከያ ፣የክልል እና የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች በጀግንነታቸው ፀንተው ባደረጉት ተጋድሎ እና በከፈሉት መስዋዕትነት የሀገራችን እና የክልላችን ሰላም ተረጋግጧል ብለዋል።

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከክልል እና ከፌደራል ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረገው የአካባቢ ጥበቃ በክልሉ ለልማት ምቹ የሰላም ሁኔታ መፈጠሩን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ በተከናወኑ የልማት ተግባራት የክልሉን አርብቶ አደር ህብረተሰብ ኑሮ መለወጥ የተቻለ መሆኑን ገልፀዋል።

የፅናት ቀንን የምናከብረው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን አጠናቀን ለምረቃ ቀን የምንጠባበቅበት ወቅት ላይ መሆኑ ታሪካዊ በዓል እንደሚያደርገውም ነው የጠቀሱት።

የአፋር ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ኮሚሽነር አህመድ ኡመድ አብደላ በበኩላቸው ሀገራችን ፈተና በገጠማት ጊዜ ፈተናውን የተሻገርነው ከኢፌዴሪ መከላከያ ጋር ተቀናጅተን እና ተባብረን በመስራታችን ነው ብለዋል።

በአፋር ክልል መዲና ሰመራ በተከበረው የፅናት ቀን ስነ-ስርዓት ላይ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ እና የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የክልል ፖሊሶች የወታደራዊ የሰልፍ ትርኢት አቅርበዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2025-10-08_21-49-49
ከጀግኖች አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር በጀግንነት ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
photo_2025-10-08_16-00-00
የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሠራዊቱን ዝግጁነት ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው።   አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም
photo_2025-10-08_21-36-23
የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት በላቀ ብቃትና ዝግጁነት የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -   ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ
photo_2025-10-06_09-06-37
ለምስራቅ ጉጂ ዞን ሠላም አሥተዋፅኦ ላበረከተው ኮር ዞኑ ምስጋና አቀረበ።
photo_2025-09-23_22-13-45
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሠራዊቱን አቅም እየገነባ ይገኛል።     ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2025-09-23_17-24-05
ሴቶች በሁሉም መስክ ፊት በመሠለፍ ውጤታማ ተግባራት ማከናወን እንዳለባቸው ተገለፀ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ