ተመራቂ መኮንኖች ማንኛውንም ተልዕኮ ለመፈፀም  ዝግጁ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም ዘርፍ ራሷን ለመቻል እያደረገች ያለችውን ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴዎች እኛ የሰራዊት አባላትና አመራሮች በእጅጉ የምንኮራባቸው ናቸው ሲሉ የመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን ተናግረዋል።

የማይታሰበውን የአባይ ግድብ ገድቦና ታላቁን የህዳሴ ግድብ ገንብቶ ማጠናቀቅ ለሀገራችን ትልቅ የድል ብስራት ነው ያሉት ጄኔራል ይመር መኮነን ሠራዊታችን ይህን የብሔራዊ ጥቅማችን ማረጋገጫ የሆነውን ግድብ ያለማቋረጥ ከወር ደመወዙ እየቆረጠ የገነባው በመሆኑ የመጠናቀቁ ዜና እጅግ አስደስቶታል ብለዋል።

ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መሠልጠን፣መደራጀትና መታጠቅ እንዳለብን እናምናለን ያሉት ጀኔራል ይመር ለዚህም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ተመራቂዎች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

እንደ ስልጠና ዋና መምሪያ በተቋሙ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ዘብ የሚቆሙ ፕሮፌሽናል አመራሮችን፣ልዩ ልዩ ሙያተኞችን እና ተዋጊዎችን ያለ ማቋረጥ በተለያዩ ማሰልጠኛዎች በማሰልጠን ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቁ የንስር ኮርስ እጩ መኮንኖች ለተከታታይ ወራቶች ሰልጥነው የመመረቂያ መስፈርቱን በወታደራዊ ስልጠናዎችና በልዩ ልዩ የግንባታ ትምህርቶች የወሰዱ በቀጣይ በመቶ አዛዥነትና በተመጣጣኝ የሀላፊነት ደረጃ ተመድበው የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ሁኔታ ሊፈፅሙ እንደሚችሉ የታመነባቸው ናቸው ብለዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2025-10-08_21-49-49
ከጀግኖች አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር በጀግንነት ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
photo_2025-10-08_16-00-00
የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሠራዊቱን ዝግጁነት ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው።   አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም
photo_2025-10-08_21-36-23
የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት በላቀ ብቃትና ዝግጁነት የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -   ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ
photo_2025-10-06_09-06-37
ለምስራቅ ጉጂ ዞን ሠላም አሥተዋፅኦ ላበረከተው ኮር ዞኑ ምስጋና አቀረበ።
photo_2025-09-23_22-13-45
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሠራዊቱን አቅም እየገነባ ይገኛል።     ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2025-09-23_17-24-05
ሴቶች በሁሉም መስክ ፊት በመሠለፍ ውጤታማ ተግባራት ማከናወን እንዳለባቸው ተገለፀ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ