ተመራቂ መኮንኖች ማንኛውንም ተልዕኮ ለመፈፀም  ዝግጁ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም ዘርፍ ራሷን ለመቻል እያደረገች ያለችውን ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴዎች እኛ የሰራዊት አባላትና አመራሮች በእጅጉ የምንኮራባቸው ናቸው ሲሉ የመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን ተናግረዋል።

የማይታሰበውን የአባይ ግድብ ገድቦና ታላቁን የህዳሴ ግድብ ገንብቶ ማጠናቀቅ ለሀገራችን ትልቅ የድል ብስራት ነው ያሉት ጄኔራል ይመር መኮነን ሠራዊታችን ይህን የብሔራዊ ጥቅማችን ማረጋገጫ የሆነውን ግድብ ያለማቋረጥ ከወር ደመወዙ እየቆረጠ የገነባው በመሆኑ የመጠናቀቁ ዜና እጅግ አስደስቶታል ብለዋል።

ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መሠልጠን፣መደራጀትና መታጠቅ እንዳለብን እናምናለን ያሉት ጀኔራል ይመር ለዚህም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ተመራቂዎች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

እንደ ስልጠና ዋና መምሪያ በተቋሙ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ዘብ የሚቆሙ ፕሮፌሽናል አመራሮችን፣ልዩ ልዩ ሙያተኞችን እና ተዋጊዎችን ያለ ማቋረጥ በተለያዩ ማሰልጠኛዎች በማሰልጠን ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቁ የንስር ኮርስ እጩ መኮንኖች ለተከታታይ ወራቶች ሰልጥነው የመመረቂያ መስፈርቱን በወታደራዊ ስልጠናዎችና በልዩ ልዩ የግንባታ ትምህርቶች የወሰዱ በቀጣይ በመቶ አዛዥነትና በተመጣጣኝ የሀላፊነት ደረጃ ተመድበው የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ሁኔታ ሊፈፅሙ እንደሚችሉ የታመነባቸው ናቸው ብለዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።