የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ አመታዊ የስራ እንቅስቃሴዎቹን አስመልክቶ የማጠቃለያ መርሃ ግብር አከናወነ።
ዋና መምሪያው በአመቱ በተለያዩ የተቋሙ ክፍሎች ያከናወናቸውን የመሠረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በፎቶ አውደ ርዕይ መልኩ አስጎብኝቷል።
በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ዋና መምሪያው የተቋሙ ሪፎርም ዋና አካል ስለመሆኑ ተናግረዋል።
የመሃንዲስ ዋና መምሪያ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ዋና መሠረት ስለመሆኑም አንስተዋል።
ሰራዊታችን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ከባድ የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል የጠላትን ሴራ በማክሸፍ የሀገራችንን ትንሳኤ ስለ ማብሰሩ ገልፀዋል።

በቀጣይም ለሀገራችን እድገት በታላቅ የዝግጁነት መንፈስና ቁርጠኝነት የበለጠ ታሪክ ለመስራት ሰራዊታችን ዝግጁ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የመሃንዲስ ዋና መምሪያው ያሉትን ጥንካሬዎች በማቀብ ለቀጣይ የተቋሙን የፕሮፌሽናል የግንባታ ሂደት የማጠናከር ተግባሩን በቆራጥነት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ዋና መምሪያው በአመቱ ለተከናወኑ አመርቂ ውጤቶች አብላጫ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ክፍሎች እና አባላቱ የሽልማትና እውቅና መርሃ ግብር አከናውኗል።
ዘጋቢ ራሔል ገዛኸኝ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official