የዩናሚስ ኢንስፔክሽን ቡድን መሪ ኮሎኔል ካርሎስ ማርኮ ግዳጅ ፈፃሚ አካል ትእዛዝ መቀበል እና መተግበር እንዴት እንደሚችል ፣ በተግባር የተልእኮ አፈፃፁም የሚፈተሽበት እና በግዳጅ ወቅት እንቅፋት ቢያጋጥም ሠላም አስከባሪ ሠራዊቱ በድርጅቱ መርህ መሠረት እንዴት መፍትሄ ማምጣት እንደሚችል በተግባር ሲያረጋግጡ ተመልክተናል ብለዋል።
ቡድን መሪው በዌስተርን ኢኳቶሪያ ያምቢዮ የተደረገ የወትሮ ዝግጅነት ማረጋገጫ የመረጃ እና ዘመቻ ቅኝት አሰራር ፣ የቋሚ እና ግዜያዊ የካምፕ ምስረታ ፣ የታገተ ሀይል ስለ ማስለቀቅ እና የአድማ ብተና የመሳስሉ ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩ አሰረድተዋል።

የ21ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ዘመቻ ሀላፊ ሻለቃ በዝየ ንጉሴ ለፍተሻው እና ቁጥጥሩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ሁሉም መገልገያ መሣሪያዎች በሚገባ መዘጋጀታቸውን ገላፀዋል። በዚህም በፍተሻው የገጠሙ ጥቃቅን ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ ውጤቱን ለማስቀጠል እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
የሻለቃው ወትሮ ዝግጅነቱ በማረጋገጥ ሂደት በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል ። በጥሩ ሁኔታ ውጤቱ እንዲጠናቀቅ የሚመለከተ ሁሉ የሻለቃዋ አባላት ከፍተኛ ርብርብ ማዳረጋቸውንም ገልፀዋል።
ዘጋቢ ፍፁም ተካ
ፎቶ ግራፍ ግርማቸው አብረሀ