ከጀግኖች አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር በጀግንነት ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።

ከጀግኖች አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር በጀግንነት  እናስቀጥላለን ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር ጄኔራል ዋኘው አለሜ ተናግረዋል።

ሜጄር ጄኔራል ዋኘው አለሜ በዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኘተው ስልጠና ላይ ከሚገኙ የሠራዊት አባላት ጋር በነበራቸው ቆይታ አባቶቻችን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበርና የህዝቦቿን ደህንነት ለማስጠበቅ ለቅኝ ገዢዎች ሳይንበረከኩ በጀግንነት ተፋልመው ያስረከቡንን ሀገር ማስቀጠልና ለሰንደቋ በመዋደቅ ሠላምን ማረጋገጥ ከዚህ ትውልድ የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል።

ሜጄር ጄኔራል ዋኘው አለሜ ጠላቶቻችን ሀገራችንን ለማፍረስ የሚፈፅሙብንን ጥቃት ለመመከትና አገራችን እንዳትደፈር ራሳችንን በስልጠና ማብቃትና ማዘጋጀት እንዲሁም የወጊያ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሀገራችንን ሠላም ለማረጋገጥና የዕድገት ጉዞዋን ለማስቀጠል የምንከፍለው መስዋዕትነት በታሪክ የሚታወስ ነው ያሉት ሜጄር ጄኔራል ዋኘው አለሜ በቀጣይም በጀግንነት፣በዓላማ ፅናትና በቁርጠኝነት የኢትዮጵያን ከፍታ ማስቀጠል ይጠበቅባችኋል ሲሉ ለሠልጣኞች አሥገንዝበዋል።

ዘጋቢ ይሁን አሻግሬ
ፎቶግራፍ እያሱ ጃርሶ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።
F
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
A1
አንድ ሆነን በአድዋ እንዳስመዘገበነው ድል በጋራ ሆነን የአክሲዮን ማህበራችንን ስኬት እናረጋግጥ፦    ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
P
በሶማሊያ ሴክተር 3 የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የ18 ወራት ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ