የአላጌ  ጀግኖች አምባና ማገገሚያ ማዕከልን የረጅም ታሪክ ማስቀጠል ተገቢ ነው።      ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የአላጌ  ጀግኖች አምባና ማገገሚያ ማዕከል ረጅም ታሪክ ያለው በመሆኑ በማዕከሉ የሚገኙ አበላት ታሪኩን በጀግንነት የማስቀጠል ሃላፊነት እንዳለባቸው ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ገልፀዋል።

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ  ይልማ በማዕከሉ በመገኘት አባላቱ የማዕከሉን ታሪክ ከማስቀጠል ባሻገር የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከምንም ጊዜ በላይ ዝግጁነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አመላክተዋል።

ማዕከሉ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና አንድነትን ለመጠበቅ ሲሉ የአካል መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን የመንከባከብ ተልዕኮውን በአግባብ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀው ማዕከሉ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ለሠራዊቱ ሞራል ከመሆን በተጨማሪ ተስፋ እንደሚሆን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ሀገርን የመበታተን እኩይ ዓለማቸውን ለማሳካት ሁሌም እንደማይተኙ የገለፁት ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ሠራዊቱ የጠላት ፍላጎትን ለማክሸፍ ዝግጁነቱን ማረገገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአላጌ ጀግኖች አምባና ማገገሚያ ማዕከል በምግብ ራስን የመቻል ተግባር እውን ለማድረግ እያከናወነ ያለው የልማት ሥራ የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል። ጀግኖችንም ጎብኝተዋል። ዘገባው የደስታ ተረፋ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።
F
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
A1
አንድ ሆነን በአድዋ እንዳስመዘገበነው ድል በጋራ ሆነን የአክሲዮን ማህበራችንን ስኬት እናረጋግጥ፦    ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
P
በሶማሊያ ሴክተር 3 የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የ18 ወራት ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ