ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ የልብ እና የደም ቧንቧ በሽታ እንዴት ይከሰታል? ህክምናውስ?

የልብ እና የደም ቧንቧዎች በተለያዩ በሽታዎች  የሚጠቁ ሲሆን፣ መንስኤያቸውም የተለያየ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
‎
‎በደም ቧንቧዎች የውስጠኛው ግድግዳ ላይ አላስፈላጊ የስብ ክምችት ሲኖር የደም ቧንቧዎች ተፈጥሯዊ ቅርፃቸውን ስለሚያጡ በቂ ደም ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ለማድረስ መቸገር የልብ እና የደም ቧንቧ በሽታን ያመላክታል።
‎
‎በስብ ክምችት የሚከሰተው በሽታ የልብ እና የደም ቧንቧ እንደሚገኝበት ቦታ እና አይነትም ይለያያል። 
‎
‎የስብ ክምችት ደምን ከልብ ወደ አዕምሮ በሚወስዱ የደም ቧንቧዎች የውስጥ ግድግዳ ላይ በመጣበቅ በቂ ደም ወደ አዕምሮ የማይሄድ ከሆነ የአእምሮ ክፍል ላይ ደም ማጣት ሊያስከትል ይችላል።
‌‎
ሲጋራ ማጨስ፣ የሰውነት ክብደት መጨመር፣ የደም ግፊት በሽታ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ የስኳር  ህመም፣ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ እድሜ እና የዘር ሀረግ በልብ እና በደም ቧንቧ በሽታ የመያዝ እድል የሚጨምሩ መንስኤዎች ናቸው፡፡

አብዛኛውን ጊዜ የልብ እና የደም ቧንቧ በሽታዎች ምንም አይነት ምልክት አያሳይም። ሆኖም ግን አንዳንዴ  የደረት መውጋት፣ የድካም ስሜት፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የሰውነት አካል በከፊል መስነፍ ‎የልብ እና የደም ቧንቧ በሽታ ምልክቶች መሆናቸው ይነገራል። 
‎
‎ለልብ እና ለደም ቧንቧ በሽታ እንድንጋለጥ የሚያደርጉ አብዛኛውን ሁኔታዎች በመከላከል ለበሽታው የመጋለጥ እድልን በቀላሉ መቀነስ ይቻላል።
‎
‎ከሲጋራ ማጨስ መቆጠብ ወይም ከሚያጨሱ ሰዎች መራቅ ፣አካላዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር ፣ የምንጠቀመውን የጨው መጠን መቀነስ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ማዘውተር እንደሚገባ ባለሞያዎች ይመክራሉ።
‎
‎ከዚህ በተጨማሪ የሰውነት ክብደት እንዳይጨምር መቆጣጠር፣ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ፣ ስብ እና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን አዘውትሮ ከመጠቀም መቆጠብ፣ ከልክ ያለፈ የአልኮል አጠቃቀምን ማስወገድ ይገባል።
‎
‎በየጊዜው የስኳር መጠን፣ የደም ግፊት እና የኮሊስትሮል እና ሌሎችንም የጤና ምርመራዎችን ማድረግ ያስፈልጋል።
‎
‎የስኳር ወይንም የደም ግፊት ህመም ካለብዎት የህክምና ክትትልዎትን በአግባቡ መፈፀም የሀኪም ምክር በትክክል መተግበር ይገባል።
‎

ወቅታዊ አጀንዳ

do
ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሁርሶ የወሰዱት ሥልጠና የአመራርነት ብቃትን እንደሚያሳድግ ገለፁ።
photo_2026-11-06_03-25-50
የኒጀር ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየምን ጎበኙ።
y
የፖለቲካ አመራሮች የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ስልጠና መውሰዳቸው የአመራር ብቃትን ያጎለብታል።       ጄኔራል ይመር መኮነን
f
ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ታሪካዊ ግንኙነታቸውንና ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ
ko
ኢትዮጵያ ለኮሪያ የከፈለችው መስዋዕትነት በኮሪያ ህዝብ ዘንድ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል፦   ሜጀር ጄኔራል ሊ ው ሄዎን
b1
6ኛ ዓመት ሰሜን ዕዝ መታሰቢያ በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ታስቧል።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።