“ድል ቁርሱ” የተሰኘው በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ የሚያንፀባርቀው መጽሐፍ ተመረቀ

       

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም

“ድል ቁርሱ” የተሰኘው በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወት ታሪክ፣ ልምድ፣ አመራር እና ጀግንነት ላይ የሚያጠነጥነው መጽሐፍ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተመረቀ።

መጽሐፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ከገጠሬዋ የኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የወታደራዊ ሕይወትን በመቀላቀል ሀገር በፈተና ማዕበል በተናጠችበት ወቅት በፅናት የቆመ ታላቅ መሪን መንፈስ የሚያሳይ እና የሕይወት ውጣ ውረድን በጥልቀት የሚያስቃኝ ነው።

በዚሁ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሮፌሰር ዳኛቸው አስፋ፣ የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብራሃ እንዲሁም አቶ ብርሃኑ ደቦጭ በመጽሐፉ ላይ ምሁራዊ ሂስ እና ዳሰሳ አቅርበዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን፣ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሸዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ