የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሃፊ ዶክተር ኦዞኒያ ኦጅሎን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት ረዳት ዋና ፀሃፊ ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ባደረጉት ውይይት ቀጠናዊ፣  አካባቢያዊና ሃገራዊ ሰላምና መረጋጋት የማጠናከር አስፈላጊነትና ትብብሮችን በሚመለከት አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ በሚከበርባቸውና በሚጠናከርበት ርእሰ ጉዳዮችም መክረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሃፊ ዶክተር ኦዞኒያ ኦጅሎ ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር የነበራቸውን ቆይታ አስመልክተውም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ ሉአላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን ለማስከበር የምታደርገውን ጥረት የመንግስታቱ ድርጅት የሚደግፈው መሆኑንና ለዚህም አላማ ስኬት ከጎኗ እንደሚቆም ዶክተር ኦዞኒያ ኦጅሎ ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ባደረጉት ውይይት አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ እንዳለበት የተናገሩት የመንግስታቱ ድርጅት ረዳት ዋና ፀሃፊ ኢትዮጵያ ድንበሬ ተጥሶብኛል ብላ ያቀረበችው ጉዳይ በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፈታት እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡

ህግና ስርአትን ማረጋገጥ ፣ የዲዲአር ሂደትን መተግበር፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸው መመለስና የህዝብ እውቅና ያለው ህገመንግስታዊ የሲቪል አስተዳደርን ወደ ቦታው በመመለስ ሂደት የመንግስታቱ ድርጅት ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆምና መንግስትን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ረዳት ዋና ፀሃፊው ዶክተር ኦዞኒያ ኦጅሎ አረጋግጠዋል፡፡

አሁን የተገኘው ሰላም በኢትዮጵያ የተጀመረውን የማህበራዊ ኢኮኖሚ የለውጥ እመርታ ለማሳደግና በሃገሪቱም የተረጋጋ ሁኔታ ለማምጣት ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለውም የመንግስታቱ ድርጅት ረዳት ዋና ፀሃፊ ዶክተር ኦዞኒያ ኦጅሎ አክለው ጠቁመዋል፡፡  

ረዳት ዋና ፀሃፊው አያይዘውም የኢትዮጵያ መንግስት ሰብዓዊና ሰላማዊ ተግባራት እንዲጠናከሩ ቁርጠኛ መሆኑንና እያደረገ ላለው ትብብርም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ዓለም አቀፍ ተቋማትም ይህን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ ከሁለት ሳምንት በፊት አዲስ አበባ መጥተው ከኢትዮጵያ መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ አካባቢያዊ ሰላም እንዲጠናከርና በሃገር ውስጥም የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲከበር የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ከጎኗ እንደሚቆም ማረጋገጣቸው ይታወሳል። ዘገባውን ያደረሰን የመከላከያ አለም አቀፍ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ነው።

ወቅታዊ አጀንዳ

do
ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሁርሶ የወሰዱት ሥልጠና የአመራርነት ብቃትን እንደሚያሳድግ ገለፁ።
photo_2026-11-06_03-25-50
የኒጀር ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየምን ጎበኙ።
y
የፖለቲካ አመራሮች የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ስልጠና መውሰዳቸው የአመራር ብቃትን ያጎለብታል።       ጄኔራል ይመር መኮነን
f
ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ታሪካዊ ግንኙነታቸውንና ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ
ko
ኢትዮጵያ ለኮሪያ የከፈለችው መስዋዕትነት በኮሪያ ህዝብ ዘንድ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል፦   ሜጀር ጄኔራል ሊ ው ሄዎን
b1
6ኛ ዓመት ሰሜን ዕዝ መታሰቢያ በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ታስቧል።

ስፖርት

do
ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሁርሶ የወሰዱት ሥልጠና የአመራርነት ብቃትን እንደሚያሳድግ ገለፁ።
photo_2026-11-06_03-25-50
የኒጀር ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየምን ጎበኙ።
y
የፖለቲካ አመራሮች የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ስልጠና መውሰዳቸው የአመራር ብቃትን ያጎለብታል።       ጄኔራል ይመር መኮነን
f
ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ታሪካዊ ግንኙነታቸውንና ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ
ko
ኢትዮጵያ ለኮሪያ የከፈለችው መስዋዕትነት በኮሪያ ህዝብ ዘንድ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል፦   ሜጀር ጄኔራል ሊ ው ሄዎን
b1
6ኛ ዓመት ሰሜን ዕዝ መታሰቢያ በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ታስቧል።

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።