ቢሾፍቱ ሞተር ቪሂክልስ ኢንጂነሪንግ ለአጠቃቀም ቀላል የሆኑ ምርቶችን እያመረተ መሆኑ ተገለፀ።

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሥር የሚገኘውን የዚህን ተቋም ሁለገብ የእንቅስቃሴ ሂደት የተመለከቱት የመከላከያ ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ፤ ኢንዱስትሪው ከነበረበት ደረጃ ተነስቶ አሁን ላለው የትርፋማነትና የቴክኖሎጂ ባለቤትነት የበቃው በአመራሩና በሠራተኛው ቁጭት በተወለደ ከፍተኛ የሥራ ተነሳሽነት መሆኑን ገልፀዋል።

ተቋሙ የላቀ ቴክኖሎጂ የታጠቁና ለአጠቃቀም ቀላል የሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ ወታደራዊ ምርቶችን በማምረት የመከላከያ ሠራዊቱ የጀርባ አጥንት መሆኑን ያሰመሩበት ሚኒስትሩ፣ የለውጥ ጎዳናውን ይበልጥ ለማስቀጠል የቅርብ ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለፅ የምርት ጥራትና የቴክኖሎጂ ዕድገቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የተገኙት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በበኩላቸው፤ ተቋሙ የለውጥ ማዕከል ሆኖ በመገኘቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፣ በተለይም በሴት ሠራተኞች ዘንድ የታየው የይቻላል መንፈስ የሚያኮራና ለሌሎችም በአርአያነት ሊወሰድ የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-10-27_02-32-52
ኢትዮጵያ እና ኳታር በወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፡፡
photo_2026-10-25_07-18-37
ለህወሃት አምስተኛ ዕድል አንሰጠውም - ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
photo_2026-10-25_07-35-07
መከላከያ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የህዳሴ ጉዞና ዘላቂ ሰላም የሚያስጠብቅ ዋስትናችን ነው::  አቶ መሃመድ እድሪስ
photo_2026-10-25_07-53-26
የኢትዮጵያ የታጠቀ ኃይል በየዘመናቱ ታሪክ እየሠራ ያለፈ ነው:: ጄኔራል ዓለምእሸት ደግፌ
photo_2026-10-25_08-18-34
ለትውልድ የሚሸጋገር ታሪክ እየሰራን መጓዛችንን እንቀጥላለን።    ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
photo_2026-10-25_08-24-55
የኢትዮጵያ ሠራዊት አይበገሬነቱን በተግባር የሚሳይ አስተማማኝ የድል ሠራዊት ነው። ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።