የጦር ኃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዛዥ ተወካይ ብርጋዲየር ጄኔራል ዶክተር ገነት ይማም ዋሽንግተን የጤና ማዕከል ለቀዶ ጥገና አገልግሎት የሚውል ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ ማበርከቱንና የሙያተኞች እገዛ ማድረጉን ተከትሎ ምስጋና አቅርበዋል።

የዋሽንግተን ጤና ማዕከል ባለቤት ዶክተር ማርቆስ ፈለቀ የጤና ማዕከሉ ሕክምና ለጦር ኃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያደረገው ዘመናዊ የቀዶ ጥገና ቁሳቀስና የሙያተኞች እገዛ የሆስፒታሉን አቅም እንደሚያሳድግ ገልፀው የሁለቱ ሆስፒታሎች ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የጦር ኃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዛዠ ፅህፈት ቤት ሀለፊ ኮሎኔል አንዳልካቸው አንዳርጌ ቀደም ካሉ ጊዝያት ጀምሮ ዋሽንግተን የጤና ተቋም ተደጋጋሚ የሙያተኞች እገዛ እና የቀዶ ጥገና ህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው በቀጣይም የእውቀት ሽግግር ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በጋራ ለማከናወን መግባባታቸውን ገልፀዋል።
