በጀግንነት የፀና፣ በድል ያሸበረቀ የሀገር ዘብ

ድል በአንድ የጦር ሜዳ ወይም በተወሰነ ጊዜ የሚገኝ ውጤት ብቻ ሳይሆን ከጀግንነት ከሀገር ፍቅርና ከህዝባዊነት የሚነሳ፣ በሙያዊ ብቃት የሚጠናከር፣ በዘመናዊ አቅም የሚገነባና በዝግጁነት የሚረጋገጥ ተቋማዊ አቅም ነው። 

የሠራዊታችን የድል ሠራዊትነትም የትላንትን ድል በመዘከር ብቻ ሳይወሰን፣ በየጊዜው ለሚፈጠሩ የደህንነት ፈተናዎች የሚመጥን አቅም በተቋም ደረጃ በቀጣይነት በመገንባቱ ነው።

ይህ ማንነት ከሠራዊቱ ጀግንነት፣ ከከፈለው መስዋዕትነትና ከፈፀመው ተልዕኮ የሚመነጭ ሀገራዊና ተቋሟዊ ትሩፋት ነው። የዛሬው ጀግንነቱ በዘመናዊ ዕውቀት፣ በቴክኖሎጂ፣ በስልጠና፣ በሙያዊ ብቃትና በተጠናከረ አመራር ለሀገራዊና ተቋማዊ አቅም አድርሶታል።

የመከላከያ ሠራዊታችን የሀገርን ሉዓላዊነትና የህዝብን ሰላም በመጠበቅ በተለያዩ የታሪክ ምዕራፎች በእሳት ተፈትኖ ወርቅነቱን ያረጋገጠ ተቋም ነው። በአስቸጋሪ ወቅቶች ያሳየው ፅናት፣ የከፈለው መስዋዕትነትና የፈፀመው ተልዕኮ ዛሬ ለተገነባው የተቋማዊ ብቃት መሠረት ሆኗል።

የድል ሠራዊትነት የአንድ የጦር ሜዳ ወይም ጊዜያዊ  ድል ብቻ ሳይሆን ተልዕኮን በብቃት መፈፀም፣ በተለዋዋጭ ሁኔታ ትክክለኛና ፈጣን ውሳኔ መስጠት፣ ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፣ ከተሞክሮ መማርና ያገኘውን ትምህርት ወደ ተቋማዊ አቅም መቀየር የድል ሠራዊትነቱ መሠረቶች ናቸው።

ድል የሚገነባው በውጊያ ወቅት ብቻ ሳይሆን ከዚያ በፊት በሚደረግ ዝግጅት ነው። ብቃት ያለው የሰው ኃይል፣ ዘመናዊ ስልጠና፣ የመረጃና የግንኙነት አቅም፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የተጠናከረ አመራር ለተገኘው ድል ዋና ምሰሶዎች ናቸው።

የሠራዊቱ የተለያዩ ተሞክሮዎችም ወደ ተቋማዊ ዕውቀት ሲቀየሩ የድል አቅሙ ይጠናከራል። የተፈፀመ ተልዕኮን መገምገም፣ የተገኘውን ትምህርት ወደ ስልጠና ማስገባት፣ የአመራር አሠራርንና አቅምን ማሻሻልና ብቃትን ወደ ዝግጁነት መቀየር የተቋም አቅም ያደርገዋል።

በዚህ አተያይ ዘመናዊነትም የድል ሠራዊትነት ዋና አካል ነው። ዘመናዊ ሠራዊት መገንባት መሣሪያን በማዘመን ብቻ ሳይወሰን፣ የሰው ኃይልን፣ የስልጠና ሥርዓትን፣ የአመራር ብቃትን፣ የመረጃ አቅምንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተቀናጀ መልኩ ማሳደግ መቻል ነው። ይህም የትላንትን ጀግንነት ከዛሬ ዕውቀትና አቅም ጋር በማጣመር ለነገ የደህንነት ሁኔታ የተዘጋጀ ተቋም እንዲገነባ አስችሏል።

የሰራዊቱ የድል አቅም ከህዝቡ ጋር ካለው ትስስርም በቀጥታ የተያያዘ ነው። ህዝባዊነት ሠራዊቱ የሚያገለግለውን ህዝብ የተልዕኮው ማዕከል አድርጎ በህግና በተቋማዊ ኃላፊነት እንዲሠራ የሚያደርግ መርህ ነው። ከህዝቡ ጋር የሚገነባው መተማመንም የተልዕኮ አፈፃፀምን የሚያግዝ ከፍተኛ አቅም ይፈጥራል።

የድል ሠራዊትነት የትላንትን ድል መዘከር ብቻ ሳይሆን፣ ድልን ማስጠበቅ የሚችል ተቋማዊ አቅምን ያለማቋረጥ መገንባት ነው። ጀግንነት የታሪክ መሠረቱ፣ ሙያዊ ብቃት የአቅሙ ምሰሶ፣ ዘመናዊነት የለውጡ አቅጣጫ፣ ዝግጁነቱ ደግሞ የተልዕኮ ስኬት መሠረቶች ናቸው።

የሀገር ዘብነት  ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር አደራ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሠራዊትም ይህን አደራ ከትላንት በተረከበው ጀግንነት፣ ዛሬ በተገነባው ዘመናዊ አቅምና ነገ በሚኖረው ዝግጁነት እያስቀጠለ ይገኛል።

የትላንት ጀግንነት መሠረቱ፣ የዛሬ ዘመናዊነት አቅሙ፣ የነገ ዝግጁነት ደግሞ የድሉ መገለጫዎች ናቸው።

ወቅታዊ አጀንዳ

SELAM
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰላም የማስከበር ተልዕኮዋን በውጤት እየፈፀመች መሆኑ ተገለፀ።
13595
ከሠራዊት ክፍሎች የተውጣጡ አመራሮች የሲቪል ወታደራዊ ትብብር የሙያ ተሞክሮ ሥልጠና ወሰዱ።
IMG_20260928_105435_619
የመከላከያ ሠራዊት የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ
IMG_20260924_161610_762
የጋራ ግብረ ኃይሉ በትብብር ያዘጋጀው 7ኛው ዙር የጋራ የልምድ ልውውጥ ሥልጠና ተሠጠ።           
IMG_20260924_134438_790
ሠላም ጠል የሆነው ህገ-ወጡ ህወሃት በለኮሰው እሳት መለብለቡን የዕዙ አዛዥ ገለፁ።
IMG_20260922_212120_128
"ድል ቁርሱ" የተሰኘው በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ የሚያንፀባርቀው መጽሐፍ ተመረቀ

ስፖርት

SELAM
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰላም የማስከበር ተልዕኮዋን በውጤት እየፈፀመች መሆኑ ተገለፀ።
13595
ከሠራዊት ክፍሎች የተውጣጡ አመራሮች የሲቪል ወታደራዊ ትብብር የሙያ ተሞክሮ ሥልጠና ወሰዱ።
IMG_20260928_105435_619
የመከላከያ ሠራዊት የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ
IMG_20260924_161610_762
የጋራ ግብረ ኃይሉ በትብብር ያዘጋጀው 7ኛው ዙር የጋራ የልምድ ልውውጥ ሥልጠና ተሠጠ።           
IMG_20260924_134438_790
ሠላም ጠል የሆነው ህገ-ወጡ ህወሃት በለኮሰው እሳት መለብለቡን የዕዙ አዛዥ ገለፁ።
IMG_20260922_212120_128
"ድል ቁርሱ" የተሰኘው በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ የሚያንፀባርቀው መጽሐፍ ተመረቀ

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።