የመከላከያ ስነ-መግባር መከታተያ መምሪያ በዓለም-አቀፍ ደረጃ ለ24ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ23ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጸረ-ሙስና ቀን በማስመልከት የአከባበር ስነ-ስርዓቱ እና አውዱ ምን ሊመሰል እንደሚችል ከባለድርሻዎች ጋር የእቅድ ውይይት አካሂዷል፡፡
ሙስና በተቋማዊ አሰራር ሂደት ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅእኖ የገለጹት የመከላከያ ስነ-ምግባር መከታተያ መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል አዲሱ ሽፈራዉ የዘንድሮው ዓለም-አቀፍ የሙስና ቀን “ስውር ትስስሮችን በማጋለጥ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ” በሚል መሪ ቃል ከህዳር 01 እስከ ህዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በፌደራል አደረጃ ሙስናን ለመከላከል የሚያስችሉ ትምህርቶችን በመስጠት ዕለቱ ተከብሮ እንደሚውል ገልፀዋል።

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ለሰራዊቱ አባላት እና ሲቪል ሰራተኞች የፀረ-ሙስና ትምህርት መስጠት፤ ሙስናን የመከላከል ተግባር የሁሉም አመራር እና አባላት ሃለፊነት መሆኑን ማስገንዘብ፤ ስለ-ስውር ጥቅም ጎጅነት በጥልቀት መወያየት እና ስልጣንን በህገ-ወጥ መንገድ መጠቀም በተልዕኮ አፈፃፀማችን ላይ ሊፈጥር የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ በማስረጃ ማስገንዘብ ዋና ዋና ተግባራት ናቸው፡፡
የኦንላይን የሃብት ማስመዝግብ ተግባራት እንደሚከናወንም ተገልጿል በዓሉ በመከላከያ ደረጃ ታህሳስ 24 ቀን 2019 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡
