ደም ምንድነው?
• ደም በማንኛውም የሰው ልጅ ሰውነት ውስጥ የሚገኝ ቀይ ፈሳሽ ሲሆን፣ አንድ ጤነኛ አዋቂ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ከ5 እስከ 6 ሊትር የሚደርስ ደም አለው።
• ሰውነታችን በየቀኑ አዳዲስ የደም ሴሎችን ያዘጋጃል። በሰውነታችን ውስጥ ያረጁ የደም ሴሎች በየጊዜው (ለምሳሌ ቀይ የደም ሴሎች በየ120 ቀኑ) እየተተኩ በቆሻሻ መልክ ይወገዳሉ።
• ደም ለመለገስ የሚፈጀው ጊዜ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ ብቻ ነው።
• ደም ለሕይወት መቀጠል ወሳኝና ምትክ የሌለው የሰውነታችን ክፍል ነው።
ደም በመለገስ የሚገኙ ጥቅሞች
• ታላቅ የሕሊና እርካታን ይሰጣል።
• በበጎ ፈቃደኝነት የሰብዓዊ አገልግሎት ተሳታፊ ያደርጋል።
• የደም ዓይነትንና አጠቃላይ የጤና ሁኔታን ያለ ምንም የገንዘብ ክፍያ ለማወቅ ያስችላል።
• ደም የሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን በደም እጥረት ምክንያት እንዳይሞቱ ሕይወታቸውን ይታደጋል።
• በሰውነት ውስጥ የብረት (Iron) መጠንን በማመጣጠን ለልብ ሕመም ያለንን ተጋላጭነት ይቀንሳል።
ደም ይበልጥ የሚያስፈልጋቸው እነማን ናቸው?
• በተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች ሳቢያ ከፍተኛ ደም ለፈሰሳቸው ሰዎች
• ከፍተኛ ቀዶ ጥገና ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች
• በተለያዩ የጤና ችግሮች ሳቢያ እንደተወለዱ አስቸኳይ ደም ለሚያስፈልጋቸው ሕፃናት
• በዘር ውርስ በሚመጡ የደም ሕመሞች (እንደ ሄሞፊሊያ እና ታላሴሚያ) ለተጠቁ ወገኖች
• በተለያዩ የውስጥ ደዌ በሽታዎች ምክንያት ከባድ የደም ማነስ ላለባቸው ሕመምተኞች
• የኬሞቴራፒ ሕክምና ለሚከታተሉ የካንሰር ሕመምተኞች
• በወሊድ ወቅት ብዙ ደም ለሚፈሳቸው እናቶች
• ከፍተኛ የቃጠሎ እና ሌሎች ከባድ የአካል ጉዳቶች ለደረሰባቸው ሰዎች ነው እናም ደም በሠለገስ የወገንን ህይወት መታደግ መታደል ነው።
