ማዕከሉ ለተቋሙ ተልዕኮ መሳካት የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ መከላከያ ምርምርና ልማት ማዕከል ከመከላከያ ክፍሎች ለተወጣጡ የምርምር ሙያተኞች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቋል።

ማዕከሉ በአጭር ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነና ፕሮጀክቶችን በማጠናከር ለተቋሙ ችግር ፈች ሥራ እየሠራ መሆኑን ያሥታወቁት የኢትዮጵያ መከላከያ ምርምርና ልማት ማዕከል ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ማዕከሉ የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት በሚፈለገው ደረጃ ጠንክሮ መሥራት ይገባዋል ብለዋል። ሠልጣኞች ከሥልጠና የተገኘውን ዕዉቀትና ተሞክሮ በሥራ ከማዋል ባለፈ ሌሎችን በማሰልጠንና በማብቃት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚገባቸው ኃላፊው  አሳስበዋል።

ሠልጣኞች በበኩላቸው በምርምር ውጤት ሽግግር፣ ምዝገባ እና በፖሊስ ቀረፃ ፣ ትንተና ፣ ዝግጅትና ትርጉም፣ በምርምር አስተዳደርና የደህንነት ጥቅሞች
እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች የተሰጠው ሥልጠና ባለን አቅም ላይ ተደማሪ ዕውቀትና ልምድ እንድናገኝ አስችሏል ብለዋል።

ለቀጣይ መሰል ሥልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን ለሠልጣኞች የዕውቅና ሰርተ-ፊኬት ተበርክቷል።

ወቅታዊ አጀንዳ

bju
ሉዓላዊነትንና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የሚችል ዘመኑን የዋጀ፣ በሙያዊ ብቃትና በቴክኖሎጂ የበቃ ሠራዊት ተገንብቷል።   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
jb
ማዕከሉ ለተቋሙ ተልዕኮ መሳካት የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ተገለፀ።
7
በኢትዮጵያ 23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ግዳጅ አፈፃፅም እተማመናለሁ ።        ሜጀር ጀኔራል ጁንሁይ ው
6
ኢንዱስትሪ ግሩፑ እና ዩኒቨርሲቲው በጋራ ለመሥራት በሚያሥችላቸው ጉዳይ ተፈራረሙ።
4
የአጠቃላይ ትምህርት መምሪያ ያሰለጠናቸውን የአንደኛ ደረጃ መምህራን አስመረቀ።
2
መምሪያው የዓለም አቀፉን የፀረ-ሙስና ቀን አከባበር አስመልክቶ ውይይት አካሄደ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።