የመከላከያ ኢንተርፕረነርሺፕ አና ኢኖቬሽን ማዕከል  በስራ ፈጠራና ክህሎት ሙያተኞችን አስመረቀ።

የመከላከያ ኢንተርፕረነርሺፕ አና ኢኖቬሽን ማዕከል  በአላጌ ጀግኖች አምባ ማዕከል በስነ ልቦና፣ በስራ ፈጠራና ክህሎት ያሰለጠናቸው ከተቋሙ በክብር የተሠናበቱ የሠራዊት አባላትን ለሶስተኛ ጊዜ አስመርቋል።
‎
‎በምረቃ ስነ- ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ኢንተርፕሪነርሺፕ አና ኢኖቬሽን ማዕከል  ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል አብደላ መሃመድ በክብር የተሰናበቱ የሠራዊት አባላት በቅድሚያ መከላከያ እንደ ተቋም ኢትዮጵያ ደግሞ እንደ ሀገር ትልቅ ክብር እንደሚሠጧችሁ በታላቅ አክብሮት ልገልፅላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።
‎
‎ሰልጣኝ ተሠናባች የሠራዊቱ አባላት በተለያዩ ሥራዎች እንዲሰማሩ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ጀምሮ ለስነ-ልቦናዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንዳይጋለጡ የሚያደርግ ስልጠና እንደሆነ ተናግረው ይህም ራሳቸውን ችለው በመደበኛነት ኑሯቸውን እንዲመሩ የሚያስችል ነው ብለዋል። በቀጣይም እናንተ ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ከክልሎችና ከሌሎች አጋሮች ጋር  በጋራ እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።
‎
‎በዕለቱ በመከላከያ የሰው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ  የቅጥርና ስንብት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ግርማ ፈዬ በክብር የተሰናበታቹሁ የሠራዊት አባላት በአገልግሎት ዘመናችሁ ያካበታችሁትን ልምድ በማከል አሁን ከተሠጣችሁ የፈጠራና ስራ ክህሎት ትምህርት በማጣመር ራሳችሁን ለመለወጥ ዝግጁ መሆን ይገባችኋል ብለዋል።
‎
‎የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የፋይናንስ ዳይሬክተር ኮሎኔል አበራ ድሪባ ለሀገራችሁ ሁሉንም ነገር የሠጣችሁ ተሠናባች ሰልጣኞች ስልጠናችሁን አጠናቃችሁ ቀጣይ ወደ ህብረተሰቡ ስትቀላቀሉ በእጅጉ የሚያግዛችሁ ነውና ከማዕከሉ ያገኛችሁት እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ ራሳችሁ ማሳደግ ይጠበቅባችኋል ሲሉ ተናግረዋል።
‎
‎የአላጌ ጀግኖች አምባ ማዕከል ኃላፊ ኮሎኔል ሚስባሁ  አረብ  ሀገራችሁ ለበርካታ አመታት በማገልገል በክብር የተሠናበታችሁ ጀግኖች የሠራዊቱ አባላት ለተሰጣችሁ ስልጠና የአላጌ ማሠልጠኛ ማዕከል ለዚሁ ምርቃት እንድትበቁ ያደረገውን ሀለንተናዊ ድጋፍ እነና  ክትትል ኩራት ይሰመዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ማስታወቂያ

No Posts Found

ወቅታዊ አጀንዳ

tem abb
ጠንካራና ዘመናዊ የመከላከያ ሠራዊት መገንባት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለቀጣናዊ ሰላም ወሳኝ ነው።  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
memin
የመከላከያ ሚኒስትሩ ለሠራዊቱ ክብርና አድናቆት ላሳየው ምክር ቤት ምስጋና አቀረቡ
mjab
የመከላከያ ኢንተርፕረነርሺፕ አና ኢኖቬሽን ማዕከል  በስራ ፈጠራና ክህሎት ሙያተኞችን አስመረቀ።
jen
'' ከስውር ትስስር የፀዳ የሎጂስቲክስ ሥርዓት ለሠራዊታችን ሁለንተናዊ ዝግጁነትና ድል ዋስትና ነው'':: ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል
et we
የሙያ ብቃትንና ዲጂታል አቅምን ማሳደግ ለተቀላጠፈ ተቋማዊ አገልግሎት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።
ym11
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር ዘመናዊ ሠራዊት መገንባቱ ተገለፀ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።