በአምስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየርሊግ በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም የተገናኙት የመቻል እና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በመቻል 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
መቻል አሸናፊ የሆነበትን ሶስት ጎሎች የፊት መስመር አጥቂዋ ትግስት ብርቄ ሰርካለም ባሳ እና ትንቢት ሳሙኤል ከመረብ አሳርፈዋል።
የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ሰባት ነጥብና ሰባት ተጨማሪ ጎል በመያዝ እየተፎካከሩ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየርሊግ ዘንድሮ በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ ናቸው።
