የሠራዊቱን የሎጂስቲክስ አቅም ለማሳደግ የትምህርት ሥርዓቱን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተሳሰር ይገባል፦     ጀኔራል ይመር መኮነን

የመከላከያ ሎጂስቲክስ ኮሌጅ የትምህርት ሥርዓቱን፣ ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር የሠራዊቱን የግዳጅ አፈጻጸም አቅም ማሳደግ እንደሚገባው የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን ገለፁ።
‎
‎ኮሌጁ በትምህርት ጥራትና በቀጣይ ተቋማዊ የሪፎርም አቅጣጫዎች ዙሪያ ከቀድሞ መምህራን፣ ተማሪዎቹና ከፍተኛ የሠራዊት አመራሮች ጋር ሰፊ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
‎
‎በመድረኩ ላይ የተገኙት የትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን ዘመናዊ ውጊያና ወታደራዊ ስምሪት በቀጥታ ከሎጂስቲክስ ዝግጁነትና ቅልጥፍና ጋር የተቆራኘ መሆኑን አንስተዋል። ኮሌጁ የሚሰጣቸውን ትምህርቶችና ሥልጠናዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ፣ የወቅቱን ዓለም አቀፋዊ ወታደራዊ ሳይንስ የሚመጥኑ ባለሙያዎችን የማፍራት ኃላፊነቱን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
‎
‎የመከላከያ ሎጂስቲክስ ኮሌጅ አዛዥ ኮሎኔል መኮንን አድማስ በበኩላቸው፣ የኮሌጁን አመሠራረት፣ ታሪካዊ ዳራና እስካሁን ያለፈባቸውን የትምህርት አሰጣጥ ሂደቶች የሚዳስስ ሰፊ ገለፃ ለታዳሚዎቹ አቅርበዋል። ባለፉት ዓመታት ለመከላከያ ሠራዊቱ የጀርባ አጥንት የሆኑ በርካታ ከፍተኛ ጀኔራል መኮንኖችን፣ የጦር መሪዎችንና ብቁ የሎጂስቲክስ ባለሙያዎችን በማፍራት ለተቋሙ ግንባታ የማይተካ ሚና መጫወቱን ገልፀዋል።
‎
‎በምክክር መድረኩ ላይ ገንቢ ምክረ-ሐሳቦችን ያቀረቡት የቀድሞ መምህራን፣ ተማሪዎችና አመራሮች፣ ኮሌጁ ዘመናዊና ሙያዊ አሠራሮችን በመዘርጋት ለተለያዩ የሠራዊቱ አሃዱዎች በዕውቀትና በክህሎት የታነጸ የተማረ የሰው ኃይል እያበረከተ እንደሚገኝ መስክረዋል።
‎
‎ተሳታፊዎች፣ የቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን ያካበቱትን ልምድ ለኮሌጁ ቀጣይ ዕድገትና ለሥርዓተ-ትምህርት መሻሻል ማዋል የሚችሉበት ቋሚ የግንኙነት መድረክ መፈጠሩ ለትምህርት ጥራቱ መረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል። መድረኩ የኮሌጁን የወደፊት የትምህርት ጥራት ደረጃ ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ጠቃሚ ግብዓቶች የተገኙበት መሆኑን ተገለጿል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-11-23_05-29-28
በእውቀት የሚመራ፣ ዘመናዊ መሣሪያዎችን የታጠቀና ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የሜካናይዝድ ኃይል ተገንብቷል         ጄኔራል ይመር መኮነን
ymer
የሠራዊቱን የሎጂስቲክስ አቅም ለማሳደግ የትምህርት ሥርዓቱን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተሳሰር ይገባል፦     ጀኔራል ይመር መኮነን
tso
ኢንስቲትዩቱ ለሁለት ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የስርዓተ ፆታ ማማከር ስልጠና ተጠናቀቀ።
fen
የኢትዮጵያ ፈንጂ ማምከን ማዕከል በፈንጂ ማጽዳት እና ማምከን ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ።
fil
የሠራዊቱን የአኗኗር ሁኔታ ለማዘመን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦  ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
desta
የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ያስገነባቸውን የክፍለ ጦር ካምፖች በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።