የኢትዮጵያ ፈንጂ ማምከን ማዕከል በፈንጂ ማጽዳት እና ማምከን ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ።

የኢትዮጵያ ፈንጂ ማምከን ማዕከል የሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተሳተፉበት በፈንጂ ማጽዳት እና ማምከን ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የመከላከያ ፈንጂ ማምከን ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ታደሰ አመሎ እንደገለጹት፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ጦርነት በተደረገባቸው የሀገራችን አካባቢዎች ተቀብረው የሚገኙ ያልተወገዱ ፈንጂዎች በማህበረሰብ ደህንነት፣ በእርሻ መሬት አጠቃቀም፣ በመሰረተ ልማት ግንባታና በኢኮኖሚ ማገገም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ ይገኛሉ።

እነዚህን ስጋቶች በዘላቂነት ለመቅረፍ ከተናጠል እንቅስቃሴዎች ባለፈ፣ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በአንድ ማዕቀፍ የሚያስተሳስር በሀገር አቀፍ ባለቤትነት የሚመራ የተቀናጀ ስትራቴጂክ እቅድ ማዘጋጀት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በስትራቴጂው ዝግጅት ሂደት ውስጥ የተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እቅድ፣ የአሰራር ጥራት፣ ለተጎጂዎች የሚደረግ ድጋፍ፣ ሀብት ማሰባሰብ፣ የተጠያቂነት ስርዓት እንዲሁም ከሀገራዊ የልማት እቅዶች ጋር ማቀናጀት የሚሉት ሰባት ቁልፍ ጉዳዮች በዋናነት ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል።

ሜጀር ጀኔራል ታደሰ አመሎ ስትራቴጂውም በተጨባጭ ሊለካ የሚችል፣ ግልጽ የአተገባበርና የሀገሪቱን ትክክለኛ ፍላጎት ያገናዘበ እንዲሆን መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት ቀደም ሲል ከነበረው በተሻለ መልኩ በትኩረት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፈንጂ ማምከን ማዕከልም ሂደቱን በቅርበት ለመምራትና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ቁርጠኛ መሆኑን አመላክተዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የዘርፉን ወቅታዊ እና አጠቃላይ ሁኔታ የሚያመላክት ገለጻ  ያቀረቡት በፈንጅ ማምከን ማዕከል ከፍተኛ የኢንፎርሜሽን ማኔጂመንት ባለሙያ የሆኑት በወይዘሮ ቅድስት ሹምበዛ በፈንጂ የተበከሉ አካባቢዎች በህፃናትና በማህበረሰቡ ላይ ባልተጠበቀ መልኩ የሚያደርሰው ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

የፈንጂ ማጽዳት ስራ ለሰላም፣ ለልማትና የሰውን ልጅ ክብር ለመጠበቅ ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይ በፈንጂ የተበከሉ አካባቢዎችን በመለየት ሁላችንም በጋራና በሀላፊነት ስሜት ማፅዳት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በወቅቱም በሀገር ውስጥ ከሚገኙና ከውጭ ሀገር በመጡ በዘርፉ ላይ ከሚሰሩ መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ጋር ቴክኖሎጂን መሠረት  ያደረገ ጠንካራ ስራ መስራት የሚያስችል ጥልቅ ውይይት ተደርጎ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

ወቅታዊ አጀንዳ

fen
የኢትዮጵያ ፈንጂ ማምከን ማዕከል በፈንጂ ማጽዳት እና ማምከን ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ።
fil
የሠራዊቱን የአኗኗር ሁኔታ ለማዘመን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦  ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
desta
የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ያስገነባቸውን የክፍለ ጦር ካምፖች በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ።
abdu
ኢትዮጵያ በዓለም ሠላምና ደህንነት ያላትን አስተዋፅኦ ለማሥቀጠልና ለማጠናከር ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባታል  - ሌተናል ጄኔራል አብዱረህማን እስማኤል
bju
ሉዓላዊነትንና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የሚችል ዘመኑን የዋጀ፣ በሙያዊ ብቃትና በቴክኖሎጂ የበቃ ሠራዊት ተገንብቷል።   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
jb
ማዕከሉ ለተቋሙ ተልዕኮ መሳካት የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ተገለፀ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።