ጠንካራና ዘመናዊ የመከላከያ ሠራዊት መገንባት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለቀጣናዊ ሰላም ወሳኝ ነው።  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛው ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ፣ ለቀጠናዊ ሰላምና ደህንነት አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችል ጠንካራ፣ ዘመናዊና በራስ አቅም የተገነባ የመከላከያ ሠራዊት መገንባቱን አረጋግጠዋል።

መከላከያ ትልቅ ስትራቴጂ ነድፎ በግልፅ ራዕይ፣ በማያቋርጥ ትጋት በቀላሉ ሸብረክ የማይል ተቋም እየገነባ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

የመከላከያ የተቋም ግንባታ በወታደራዊ አቅም ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በጠንካራ ኢኮኖሚ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በራስ የመቻል አቅም ላይ የተመሠረተ መሆኑንም አንስተዋል።

የሰራዊቱን ዩኒፎርም፣ የምግብ፣ የመሣሪያና የተለያዩ የድጋፍ ግብዓቶች በራስ አቅም ማምረት፣ መጠገንና ማቅረብ የተቋሙን ነፃነትና ዘላቂነት ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል።

የሰራዊቱ ዝግጁነት በተከታታይ ስልጠናና ተግባራዊ ልምምድ መገንባት እንዳለበት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣  የዘመኑ የጦርነት አካሄድ በፍጥነት እየተለወጠ በመሆኑ ሰራዊቱ አዳዲስ የቴክኖሎጂ፣ የመረጃና የኦፕሬሽን አካሄዶችን መረዳትና መተግበር እንዳለበትም አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ የሕዝብ ብዛትና የኢኮኖሚ አቅም በማንሳትም በቀጠናው ያላት ሚና ትልቅ መሆኑን ያመላከቱት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዝግጅታችን ከጂኦግራፊ የራቁና ሀገራችንን ለመውረር የሚፈልጉ አካላት ካሉ በተሟላ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙም አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ የተዘጋጀ ህዝብ፣ የተደራጀ ሰራዊት፣የተባበረ ልብ ያለው ማህበረሰብ ስላላት እንደሀገር ለመፅናት የሚያስችል ቁመና ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፣ ይህም የተገኘው መተኪያ የሌላትን ህይወታቸውን ሊገብሩ በፈቀዱና በወደዱ ጀግኖች መሆኑንም አውስተዋል። የአሁኑ ትውልድም ይህን የማስቀጠል ታሪካዊ ሀላፊነት ያለበት ትውልድ መሆኑንም አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት ህይወቱን ለሚገብር ሰራዊት ተገቢውን ከብር መስጠት፤ ለጀግኖች ሰማዕታት፣ አካላቸው ለጎደለና ለደከሙ ሁሉ ያለው ትርጉም ከፍተኛ ነው።

ጠንካራና ዘመናዊ መከላከያ ሠራዊት መገንባት የአገርን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለመጠበቅ፣ የሕዝብን ደኅንነት ለማረጋገጥና ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የሰላምና የደኅንነት ሚና ለመወጣት ወሳኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

ማስታወቂያ

No Posts Found

ወቅታዊ አጀንዳ

tem abb
ጠንካራና ዘመናዊ የመከላከያ ሠራዊት መገንባት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለቀጣናዊ ሰላም ወሳኝ ነው።  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
memin
የመከላከያ ሚኒስትሩ ለሠራዊቱ ክብርና አድናቆት ላሳየው ምክር ቤት ምስጋና አቀረቡ
mjab
የመከላከያ ኢንተርፕረነርሺፕ አና ኢኖቬሽን ማዕከል  በስራ ፈጠራና ክህሎት ሙያተኞችን አስመረቀ።
jen
'' ከስውር ትስስር የፀዳ የሎጂስቲክስ ሥርዓት ለሠራዊታችን ሁለንተናዊ ዝግጁነትና ድል ዋስትና ነው'':: ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል
et we
የሙያ ብቃትንና ዲጂታል አቅምን ማሳደግ ለተቀላጠፈ ተቋማዊ አገልግሎት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።
ym11
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር ዘመናዊ ሠራዊት መገንባቱ ተገለፀ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።