የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ብላቴ በመገኘት የ4ኛ ዙር መሠረታዊ ውትድርና ስልጠናን በማስጀመር የ44ኛ ዙር የኮማንዶ ሰልጣኞችን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።
ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ በዲስፕሊን የታነፀ ትክክለኛ ፅናትን የተላበሰ አገራዊ ፍቅር ያለዉ ኢትዮጵያዊ ሰራዊት የሚገነባበት እና ሰልጥኖ የሚወጣበት ትልቅ ማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑን የገለፁት ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ እናንተም የአሰልጣኞችን የካበተ አቅም በመጠቀም በዲስፕሊን የታነፀ ጠንካራ እና አገራዊ ፍቅርን የተላበሰ ወታደር እና ኮማንዶ ለመሆን ጠንክራቹህ መስራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

ኮማንዶ ማለት በታማኝነት እና በቅንነት ራሱን አሳልፎ በመስጠት ለአገሩም ለህዝቡም አኩሪ ታሪክ የሚሰራ የዉጊያ ማርሽ ቀያሪ የተበላሸ ዉጊያን በአጭር ሰዓት በመድረስ ዉጊያ የሚያስተካክል የዘገዩ ዉጊያዎችን የሚያፋጥን ጀግና ነዉ ፤ እናንተም የዚህ ክፍል አባል ለመሆን ፈቅዳችሁ መምጣታችሁ ደስ ያሠኛልና ጠንክራችሁ ሠልጥኑጨሲሉ አበረታትተዋል።
አገራችን ወደ ከፍታ እየተጓዘች ነዉ ለዚህ እድገት እና ከፍታ ደግሞ የሰራዊታችን ሚና የጎላ ነዉ ያሉት አዛዡ እንደ ሃገር በተሰሩ የልማት ስራዎች ከኪሱ ገንዘብ አዉጥቶ ቦንድ ከመቁረጥ ጀምሮ በጉልበቱ እስከ መስራት እንዲሁም የሚሰሩ አገራዊ ልማቶች ደህንነታቸዉ ተጠብቆ እንዲጠናቀቁ እስከ ህይወት መስዋዕትነት የደረሰ አበርክቶ ማድረጉንም አንስተዋል።

በተቋሙ ዉስጥ የሙያ ባለቤት የሚያደርጉ እድሎች መኖራቸዉን የገለፁት ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ ዉትድርና ሲነሳ ጦርነትን ብቻ ማሰብ ስህተት ነዉ ስለዚህ ራሳችሁን በማብቃት እና በማሳደግ የሙያ ባለቤት ሆናችሁ ለትዉልድ የሚሻገር ተግባርን በማከናወን አገራችሁንና ራሳችሁን የሚለዉጥ ይጠበቅባችኋል በማለት አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ ምህረት ስመኝ
ፎቶ ግራፍ አብዱራማን ሃሰን
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official





