ከሃገር ባለፈ በአለም አቀፍ ደረጃ ሰላምን ለማፅናት በቁርጠኝነት እየሰራ ያለ የማይበገር የድል ሰራዊት።

በዩናሚስ ደቡብ ሱዳን ጃንግሌ ስቴት የተሰማራው የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ 118ኛው የሰራዊት ቀንን የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት
በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኩነቶች አክብሯል።

‎የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለሃገር ሉዓላዊነትና ለህዝቦች ህልውና መከበር በተግባር እየከፈለ ባለው መስዋዕትነት ሃገርን ከማፅናት ባሻገር በአለም አቀፍ ደረጃ ሰላምን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ያለ የማይበገር የድል ሰራዊት ነው ብለዋል።

‎በትውልድ ቅብብሎሽ ላለፉት 118 አመታት በበርካታ ውስብስብ ሂደቶች ውስጥ የተሻገረ፣ በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሰራዊት ታሪክ ውስጥ የሃገርን ህልውና አስጠብቆ ለማቆየት ውድ ዋጋ ለመክፈል የማይሰስት፣ የማይነጥፍ ህያው ታሪክ ያለው፣ ህዝባዊ መሠረትን የያዘ ዘመን ተሻጋሪ የመከላከያ ሰራዊት መገንባቱንም አውስተዋል ዘጋቢ አንዋር ሁሴን ነው

በተመሳሳይ የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት በሚል መሪ ቃል 118ኛ የሠራዊት ቀን አክብሯል።

በያምቢዮ ካምፕ በተደረገ ዝግጅት የተገኙት የሻለቃዋ አዛዥ ኮሎኔል እንዳለ እሸቱ ለሀገር አንድነት ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉ ወታደሮችን ማሠብ እንደሚገባ ጠቁመው ሠራዊቱ ከአባቶቹ የተረከባት ሀገር በማንም እንዳትደፈር ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት ተናግረዋል።

በሴክተር ሳውዝ ጁባ ደሩፒ ካምፕ በነበረ አከባበር የሻለቃዋ አስተዳደር ሌተናል ኮሎኔል ወርቁ አሸናፊ የተሠጠን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት የሠላም አምባሳደርነታችን በማስቀጠል የሀገራችንን ጥቅም እና ክብር ማስጠበቅ ይገባናል ብለዋል ዘጋቢ ፍፁም ተካ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

FDRE Defense Force – የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት, [10/26/2025 12:05 PM]
መከላከያ ሠራዊት ሀገሩን በመስዋዕትነት ያፀና የሀገር ዘብ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም

የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ ሃሳብ 118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን ቢሾፍቱ በሚገኘው የባህር ኃይል የስልጠና ማዕከል በተከበረበት ዕለት የበዓሉ ታዳሚዎች የተሰማቸውን ደስታና ኩራት ገልፀዋል።

በዝግጅቱ የተዳሙ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች መከላከያ ሠራዊታችን ሀገሩን በመስዋዕትነት እያፀና በድርብ ድል ታጅቦ የዛሬው ቀን መድረሱ የሚያኮራና የሚያስደስት መሆኑን ተናግረዋል።

ሠራዊታችን ለሀገራችን ኢትዮጵያ የከፈለው ውለታ በወርቅ ብዕር በደማቁ በታሪክ መዝገብ ላይ ሰፍሮ የሚኖር መሆኑን የገለፁት አስተያየት ሰጭዎች በቀጣይ በሌላ ድልና ሞገስ ታጅበን እንደምንገናኝ ትልቅ ተስፋ የሰነቁ መሆኑን ገልፀዋል።

ለመላው የመከላከያ ሠራዊትና ለቤተሰቦቹ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ወዳጆች የእንኳን አደረሳችሁ መልክትም አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ ማሙሸት አድነው
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።