መቻል ኢትዮጵያንና ሠራዊቱን ወክሎ በአፍሪካ መድረክ ለመወዳደር ተዘጋጅቷል።

የመከላከያ መቻል የእጅ ኳስ ቡድን በአንጎላ በሚካሄደው 47ኛው የአፍሪካ ክለቦች የእጅ ኳስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያንና ተቋሙን ወክሎ ለመወዳደር ያደረገውን የቅድመ-ውድድር ዝግጅት ማጠናቀቁን የክለቡ ሥራ አስፈጻሚ ገልፀዋል።

የመቻል ስፖርት ክለብ ስራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም በቡድኑ ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን በመቅረፍና ወጣት ተጫዋቾችን ከሠራዊቱና ከሲቪል ማህበረሰቡ በማቀናጀት ቡድኑን ማጠናከር ተችሏል።

መቻል የአዲስ አበባ ዋንጫን በማሸነፍና በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ በአህጉራዊው ውድድር የመሳተፍ ዕድል ማግኘቱንም ገልጸዋል።

በአንጎላ በሚካሄደው ውድድር የሠራዊታችንን ጥንካሬና አልሸነፍ ባይነት ለማሳየት እንሠራለን ያሉት ጀነራል መኮንኑ ኢትዮጵያንና ሠራዊቱን ወክለን ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ተዘጋጅተናል ብለዋል።

የመቻል የእጅ ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሻለቃ ባሻ ደጀኔ ካሳይ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ክለቦች የእጅ ኳስ ሻምፒዮና ሊግ ከፍተኛ ፉክክር የሚካሄድበት ውድድር መሆኑን ጠቁመው ቡድኑ ከዚህ ቀደም በሞሮኮ በተካሄደው ውድድር በመሳተፍ ያገኘው ልምድ ለዘንድሮው ውድድር ጠቃሚ መሆኑንና ዘንድሮ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በበቂ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

የመቻል የእጅ ኳስ ቡድን ተጫዋቾችም በአንጎላ፣ ሞሮኮና ኡጋንዳ በተካሄዱ ውድድሮች በመሳተፍ ያገኙት አህጉራዊ ልምድ ለውድድሩ ያላቸውን ዝግጅት እንዳጠናከረ ተናግረው በውድድሩ የተሻለ ውጤት ለማምጣት መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል።

ዘጋቢ አብርሃም ዘርጋው
ፎቶ ግራፍ ጀረመው ጨሬ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

IMG_20260928_105435_619
የመከላከያ ሠራዊት የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ
IMG_20260924_161610_762
የጋራ ግብረ ኃይሉ በትብብር ያዘጋጀው 7ኛው ዙር የጋራ የልምድ ልውውጥ ሥልጠና ተሠጠ።           
IMG_20260924_134438_790
ሠላም ጠል የሆነው ህገ-ወጡ ህወሃት በለኮሰው እሳት መለብለቡን የዕዙ አዛዥ ገለፁ።
IMG_20260922_212120_128
"ድል ቁርሱ" የተሰኘው በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ የሚያንፀባርቀው መጽሐፍ ተመረቀ
IMG_20260922_212119_606
ኢትዮጵያ ትልቅ ክብር ሰጥታኛለች፥ ለሀገሬ የምሰስተው ነገር የለም - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።