ከሠራዊት ክፍሎች የተውጣጡ አመራሮች የሲቪል ወታደራዊ ትብብር የሙያ ተሞክሮ ሥልጠና ወሰዱ።

የልምድ ልውውጡ የመከላከያ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት እና በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ግብረ ኃይል ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በዘርፉ ያሉ ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ የሠራዊቱን የተልዕኮ አፈፃፀም ለማጠናከር ያለመ ሥልጠና መሆኑም ተገልጿል።

በልምድ ልውውጥ ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የወታደራዊ ጉዳዮች ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ዛካሪ ኤ ማካርተር እንዳሉት ከመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር በተካሄደው ውይይት በማህበረሰብ ግንኙነት፣ በተፈናቃዮች አያያዝ፣ በሲቪል መረጃ መሰብሰብ ላይ ያተኮረ ነው።

ይህንን መረጃ በወታደራዊ ተልዕኮዎች ውስጥ በማቀናጀት ዙሪያ ያሉ ሙያዊ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን መለዋወጥ የሠራዊት ተልዕኮን በብቃት ለማሳካትና ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ጠቃሚ እንደሆነም ገልፀዋል።

ሠልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ተሞክሮ በቀጣይ ሥራዎቻቸው ተግባራዊ በማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ቅንጅት ለማጠናከር እና የተልዕኮ አፈጻጸምን ለማሻሻል እንደሚጠቀሙበትም የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

የሙያ ተሞክሮ ልውውጡ የመከላከያ ሠራዊቱን የሲቪል ወታደራዊ ትብብር አቅም በማጎልበት በሠላም ማስከበር፣ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በተለያዩ ተልዕኮዎች ወቅት ከማህበረሰቡ ጋር የሚደረገውን ቅንጅት በማጠናከር የተልዕኮ ውጤታማነትን ለማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-10-19_07-48-18
የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ቀጠናዊ ፀጥታና ደህንነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አላቸው።
photo_2026-10-19_05-25-42
የሚገጥሙ ፈተናዎችን በድል ለመሻገር የመከላከያ አቅምን ማጠናከር ያስፈልጋል - አቶ ጌታቸው ረዳ
photo_2026-10-19_03-44-25
ኢትዮጵያ በወታደራዊ ዲፕሎማሲ ሀገራዊ እውነታን ለዓለም በማስገንዘብ የላቀ ስኬት አስመዝግባለች፦     ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ
photo_2026-10-16_07-10-29
የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ ኢድሪስ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ
photo_2026-10-16_06-58-03
በአለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ለሚሰማሩ መኮንኖች ስልጠና ተሰጠ።
photo_2026-10-16_06-31-08
የናይጄሪያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ልዑክ በኢትዮጵያ መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ጉብኝት አደረጉ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።