በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል የአለም አቀፍ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እና በፈረንሳይ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በጋራ ባዘጋጁት በአለም አቀፍ የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮና ህጎች ፣በሰብአዊ መብት አያያዝ እና የተለያዩ ኮርሶችን ያካተተ በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና ለሁለት ሳምንት ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ማጠቃሊያ ላይ በመገኘት ለተመራቂዎች ሰርተ-ፊኬት የሠጡት በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል የአለም አቀፍ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ገዛኸኝ ፍቃዱ ሰልጣኞች በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር በወሰዳችሁት ስልጠና መሠረት በምትሰማሩበት ግዳጅ በተሻለ ደረጃ ውጤታማ ስራዎችን መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በኢንስቲትዩቱ እና በፈረንሳይ መንግስት በቂ ዝግጅት ከማድረግ በተጨማሪ በአሰልጣኞችና በሰልጣኞች ጠንካራ ተሳትፎ ውጤታማ እና ግቡን ያሳካ ስልጠና መሰጠቱንም ገልፀዋል፡፡ ለስልጠናው መሳካት ድጋፍ ላደረጉ ለፈረንሳይ መንግስት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ምክትል የመከላከያ አታሼ የሆኑት ሌተናል ኮሎኔል ዮሴፍ ሪቻርድ ስልጠናው አሳታፊና ሆኖ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር ያሥቻለ መሆኑን ጠቁመው ለቀጣይ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን እና የፈረንሳይ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የሜቲ ጌታቸው ነው
