ወታደራዊ ታሪክን፣ የሀረር አካዳሚን ታሪክና የጦር ሠራዊቱን ታሪካዊ አሻራ የሚያሳዩ የተለያዩ ወታደራዊ አሻራ ያረፈባቸው መጻሕፍት፣ የትምህርት ማኑዋሎችና ታሪካዊ ቅርሶችን ለወታደራዊ ቅርስና ሙዚየም አስተዳደር ማዕከል የማሥረከብ መሮሃ ግብር ተካሂዷል።
የኢህዲሪ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት ሌተናል ኮሎኔል ፍስሃ ደስታ በዘመናቸው ሲማሩባቸውና ሲያነቧቸው የቆዩት የተልያዩ መፅሐፍቶችን በባለቤታቸው ወይዘሮ አረገወይን ገብረስላሴ ለወታደራዊ ቅርስና ሙዚየም አስተዳደር ማዕከል ኃላፊ ሜጄር ጄነራል ጥሩዬ አሰፌ አሥረክበዋል።
ከወታደራዊ ታሪክ ጋር ተያያዥነት ያላቸው 19 በአማርኛ የተጻፉ መጻሕፍት፣ ስለ ሀረር አካዳሚ የተለያዩ 31 የትምህርት ማኑዋሎች፣ 33 በእንግሊዝኛ የተጻፉ የመስክ መመሪያ መጻሕፍት (Field Manuals) እና ሌሎችም ተካተዋል።
ከወታደራዊ ታሪክ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ቅርሶችና መፅሐፍቶችን በጥንቃቄ አቆይተው ማዕከሉ በማሥረከባቸው ከሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሠፌ ምስጋና ተችሯቸዋል።
