የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ግብረ ኃይል ጋር በትብብር 7ኛው ዙር የጋራ የልምድ ልውውጥ ሥልጠና ተሰጥቷል።
ሥልጠናው ከተለያዩ የሠራዊት ክፍሎች ለተውጣጡ አመራሮችና አባላት የተሰጠ ሲሆን፣ በዘመናዊ የመገናኛና የመረጃ ቴክኖሎጂ ሥርዓቶች ላይ ያተኮረ ነው።

በስልጠናው ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ የመከላከያ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ማቲው ኮፕ፣ ሥልጠናው በተሳታፊ ሀገራት መካከል የልምድና የእውቀት ልውውጥን በማጠናከር የጋራ አቅምና ትብብርን ለማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ የመከላከያ ተቋሙን የመገናኛ አውታረ መረብ ብቃት ማሳደግ፣ የመረጃ ፍሰትን ማፋጠን እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን ማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።

ባለሙያዎች እንደገለፁት ስልጠናዎች የተቋሙን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና ተግባራዊ ብቃት በማጠናከር ለሀገራዊ ደህንነት ያለውን አስተዋጽኦ ያጎለብታሉ።
ዘጋቢ ታድላ መላኬ
ፎቶግራፍ ጌታሰው ጌትነት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
