የልምድ ልውውጡ የመከላከያ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት እና በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ግብረ ኃይል ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በዘርፉ ያሉ ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ የሠራዊቱን የተልዕኮ አፈፃፀም ለማጠናከር ያለመ ሥልጠና መሆኑም ተገልጿል።
በልምድ ልውውጥ ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የወታደራዊ ጉዳዮች ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ዛካሪ ኤ ማካርተር እንዳሉት ከመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር በተካሄደው ውይይት በማህበረሰብ ግንኙነት፣ በተፈናቃዮች አያያዝ፣ በሲቪል መረጃ መሰብሰብ ላይ ያተኮረ ነው።
ይህንን መረጃ በወታደራዊ ተልዕኮዎች ውስጥ በማቀናጀት ዙሪያ ያሉ ሙያዊ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን መለዋወጥ የሠራዊት ተልዕኮን በብቃት ለማሳካትና ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ጠቃሚ እንደሆነም ገልፀዋል።

ሠልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ተሞክሮ በቀጣይ ሥራዎቻቸው ተግባራዊ በማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ቅንጅት ለማጠናከር እና የተልዕኮ አፈጻጸምን ለማሻሻል እንደሚጠቀሙበትም የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
የሙያ ተሞክሮ ልውውጡ የመከላከያ ሠራዊቱን የሲቪል ወታደራዊ ትብብር አቅም በማጎልበት በሠላም ማስከበር፣ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በተለያዩ ተልዕኮዎች ወቅት ከማህበረሰቡ ጋር የሚደረገውን ቅንጅት በማጠናከር የተልዕኮ ውጤታማነትን ለማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።
