የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ ኢድሪስ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ ኢድሪስና ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ሎሚ በዶ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተቋማዊ ሪፎርም፣ በትምህርትና ሥልጠና፣ በምርምር እና በመከላከያ ቴክኖሎጂ ልማት እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብርጋዲየር ጀነራል ከበደ ረጋሳ ዩኒቨርሲቲው ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ባከናወናቸው የሪፎርም ሥራዎች፣ በትምህርትና ሥልጠና ጥራት፣ በምርምር ውጤቶች፣ በመከላከያ ቴክኖሎጂ ፈጠራና በዓለም አቀፍ ትስስር የተመዘገቡ ዋና ዋና ውጤቶችን በዝርዝረ ገለፃ አቅርበዋል።

በገለፃው የዩኒቨርሲቲው ቀጣይ የልማት አቅጣጫዎችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በኘሬዝደንቱ ተመላክተዋል። ከእነዚህም መካከል የትምህርትና ምርምር መሠረተ ልማትን ማሻሻል፣ ለጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማስተማሪያ ሆስፒታል ማቋቋም፣ የሠራዊቱን የሰው ኃይል የትምህርት ተደራሽነት ማስፋፋት፣ የሰው ኃይል ልማትን ማጠናከር፣ ለምርምር በቂ ድጋፍ ማሟላትና የምርምር ውጤቶችን ወደ ተግባር ማሸጋገር ይገኙበታል።

ሚኒስትሩ አቶ መሀመድ ኢድሪስ አጠቃላይ የተመለከቱት የስራ አፈፃፀም ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ተቋም ከመሆን ባለፈ፣ ለመከላከያ ሠራዊቱ ብቁ የሰው ኃይል የሚያፈራ፣ የምርምር ውጤቶችን ወደ ተግባር የሚቀይርና የሀገር ውስጥ የመከላከያ ቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ የሚሠራ ስትራቴጂያዊ ተቋም መሆኑን እንዳረጋገጠላቸው ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ የመከላከያ ትምህርት ተቋም ዘላቂ ስኬት የሚለካው በተመረቁ ተማሪዎችና በተከናወኑ ምርምሮች ብቻ ሳይሆን፣ ውጤቶቹ ለሠራዊቱ የተልዕኮ አፈጻጸምና ለሀገራዊ የመከላከያ አቅም በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ጭምር ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው በዘመናዊ ማዕከላዊ ላቦራቶሪ በሚሰጣቸው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣ በግብርና፣ በመኖ ማቀነባበርና በችግኝ ልማት ያሳየውን አበረርክቶ በማድነቅ፣ የገቢ ማስገኛ አቅሙን የሚያሳድጉ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ መሐመድ ኢድሪስ አሳስበዋል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በበኩላቸው የተቋማዊ ሪፎርሙን በዘላቂነት ማጠናከር ፣ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ፣ የምርምር ውጤቶችን ወደ ተግባር ማሸጋገርና የቴክኖሎጂ ፈጠራን ማበረታታት ለቀጣይ ሥራዎች ቁልፍ አቅጣጫዎች በመሆናቸው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
ዘገባው የዩኒቨርሲቲው ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-10-16_07-10-29
የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ ኢድሪስ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ
photo_2026-10-16_06-58-03
በአለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ለሚሰማሩ መኮንኖች ስልጠና ተሰጠ።
photo_2026-10-16_06-31-08
የናይጄሪያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ልዑክ በኢትዮጵያ መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ጉብኝት አደረጉ።
photo_2026-10-14_03-46-06
ፋታ ሲገኝ  .........
photo_2026-10-13_12-31-12
ከወታደራዊ ታሪክ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ለማዕከሉ ተበርክቷል።
SELAM
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰላም የማስከበር ተልዕኮዋን በውጤት እየፈፀመች መሆኑ ተገለፀ።

ስፖርት

photo_2026-10-16_07-10-29
የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ ኢድሪስ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ
photo_2026-10-16_06-58-03
በአለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ለሚሰማሩ መኮንኖች ስልጠና ተሰጠ።
photo_2026-10-16_06-31-08
የናይጄሪያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ልዑክ በኢትዮጵያ መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ጉብኝት አደረጉ።
photo_2026-10-14_03-46-06
ፋታ ሲገኝ  .........
photo_2026-10-13_12-31-12
ከወታደራዊ ታሪክ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ለማዕከሉ ተበርክቷል።
SELAM
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰላም የማስከበር ተልዕኮዋን በውጤት እየፈፀመች መሆኑ ተገለፀ።

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።