ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ሁሉ በጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነት አሸንፋ ፀንታ ትቀጥላለች።  ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

ኢትዮጵያ በአሻጥረኞች የሚገጥሟትን ፈተናዎች ሁሉ በጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነት አሸንፋ ፀንታ ትቀጥላለች ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

አዛዡ ከጠቅላይ መምሪያው ስታፍ የሠራዊት አባላት ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ በርካታ አሻጥሮች መኖራቸውን ጠቁመው ህልውናዋን የሚፈታተኑ ሠላም ጠል ኃይሎችን አደብ እንዲገዙ እያደረግን እንገኛለንም ብለዋል።

ባዳዎች ባንዳዎችን በመጠቀም በጦርነት ውስጥ እንድንቆይ ይፈልጋሉ ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ  አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በመስዋዕትነታችን የባዳውንና የባንዳውን ሴራ አክሽፈናል ሲሉም ተናግረዋል።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ኢትዮጵያ በባዳና ባንዳ አሻጥር ያጣችውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ እንዲሁም የጀመረችውን ጉዞ ለማሳካት በምትወስዳቸው እርምጃዎች በሁለንተናዊ መስክ የሠራዊቱ ዝግጁነት ከመቼውም ጊዜ የላቀ
ስለመሆኑም አረጋግጠዋል።

የወታደር ክብሩ ሀገር ማቆየት ነው ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ  ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ እኛ የቆምነውም የምንሞተውም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ  ጥቅምና ለህዝቦቿ ክብር ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ተቋማችን ኢትዮጵያና ብሔራዊ ጥቅሟን ለመጠበቅ በሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ የሠራዊቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝም አንስተዋል።

ሰሜን ምዕራብ ዕዝ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ተልዕኮ በተሰጠው ፅንፈኛው ቡድን ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል ያሉት አዛዡ የቀጠናውን ሠላም አስተማማኝ ለማድረግ በሚደረገው ስምሪት እንደ ስታፍ፣ አስተማማኝ ድጋፍ የመስጠት ተልዕኳችሁን አጠናክራችሁ መቀጠል ይጠበቅባችኋል ሲሉም አሳስበዋል።  ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2025-11-03_16-04-30
ሠራዊቱ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣ የሚችል ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ ነው።   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
AS
ሠራዊቱ በከፈለው መስዋዕትነት የቀጠናው ሠላም ተረጋግጧል።    ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን
B
ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ሁሉ በጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነት አሸንፋ ፀንታ ትቀጥላለች።  ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
16
ሰላም ፣ ልማትና የባህር በር ባለቤትነታችንን እናረጋግጣለን!!    ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ 
13
ዛሬ ኩሩ ሀገርን ለሚጠብቅ ኩሩ ኃይል የሚገባውን ክብር የምንሰጥበት ታላቅ ቀን ነው    ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
10
የኢትዮጵያ የባህር ሀይል የሚሰጠውን ግዳጅ ለመወጣት የሚያስችል ሁለንተናዊ ቁመና ላይ ይገኛል።     ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ