የቤኒ ሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ክልል አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ከምዕራብ ዕዝ ኮማንድና ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም ከክልሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በዚህ ወቅት ሠራዊቱ መስዋዕትነት በመክፈል የክልሉንና ሀገራዊ ሠላምን እያረጋገጠ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን ተናግረዋል።
ክልሉ የተለያዩ ፀረ-ሠላም ሀይሎችና ሰርጎ ገቦች እንቅስቃሴ የሚስተዋልበት አካባቢ ቢሆንም በሰራዊቱ የጀግንነት ተጋድሎ ሴራቸው እየመከነ መሆኑን የገለፁት አቶ አሻደሊ ሀሰን፤ ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ ሠራዊቱ በሚያደርገው ሁለንተናዊ ጥረት የክልሉ መንግስትና ህዝብ የበኩሉን ሚና ለመጫወት ሁሌም ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል አማረ ባህታ በበኩላቸው፤ ምዕራብ ዕዝ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ አሸባሪውን ሸኔንና ፅንፈኛውን ፋኖ እንዲሁም ሌሎች ፀረ-ሠላም ሀይሎችን የመደምሰስ ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ እየፈፀመ መሆኑን ገልፀዋል።
ዓላማችንና ግባችን ኢትዮጵያን ማፅናት ነው። በመሆኑም ከዚህ ቀደም በግዳጅ ቀጠናችን ከሚገኙ ከአካባቢው መስተዳድር አካላት፣ ሌሎች የፀጥታ ኃይሎችና የአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት ያስመዘገብናቸውን ድሎች በማጎልበት ለህዝባችን ሠላምና ልማት ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ተልዕኳችን ለመወጣት ቀን ከሌት እንሰራለን ብለዋል።
አዛዡ የኢትዮጵያን ልዕልናና የህዝቦቿን ሠላም ለማናጋት ሴራ ሲጎነጉኑ ውለው የሚያድሩ የጥፋት ኃይሎች የፈለጉትን ያክል ቢፍጨረጨሩም ከመላው ህዝባችን ጋር ሆነን ፈተናዎችን ተሻግረን ድል እናሥመዘግባለን ነው ያሉት።
የምዕራብ ዕዝ እና የክልል ባለድርሻ አካላት ቀጣይ የፀጥታ የስራ አቅጣጫዎችንም አስቀምጠዋል።
ዘገባው የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
													
													
													




